ዜና

ዜና፡ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን ያሳለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ እና አገራዊ ምስቅልቅልን የሚያስከትል ነው _ ኢዜማ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) መንግሥት የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን ያሳለፈው ውሳኔ በየትኛውም መለኪያ ወቅቱን ያልጠበቀ እና ሃገራዊ ምስቅልቅልን የሚያስከትል ነው ሲል ገለጸ:: 

ፓርቲው መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ ትላንት ባወጣው የአቋም መግለጫ፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው የኑሮ ውድነትን በማባባስ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል ገልጿል::

“የውጭ ምንዛሬን በገበያ መወሰንን በሚመለከት በተወሰነው ውሳኔ የሚመጣውን ማንኛውም በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርስ የምጣኔ ሀብት፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል” ሲልም ኢዜማ አስገንዝቧል።

አሁን መንግሥት የወሰደው እርምጃ የኑሮ ውድነትን በማባባስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚከት መሆኑን ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በግልፅ መመልከት ይቻላል ያለው መግለጫው አክሎም መንግሥት የደሞዝ ጭማሪ: ድጎማ እና ሌሎች ድጋፎችን አደርጋለሁ ማለቱ ጊዜያዊ ማስታገሻ እንጂ ለዘለቄታው መፍትሔ አይሆንም ሲል ገልጿል::

እንደሃገር ምርታማነትን ማሳደግ ለገባንበት ኢኮኖሚያዊ ስብራት መጠገኛ ነው ሲል የገለጸው ኢዜማ አክሎም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ እንቅፋት የሆነውን የሰላም እጦት እና የሃገሪቱን ውስብስብ “የዘውጌ ፌደራሊዝም” ፖለቲካ መፍትሔ ማበጀት እንደሚገባ አስስቧል::

“እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የዓብይ ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መግባቷን›› በማስመልከት የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው እንዲወሰን በተደረገ ማግስት ምጣኔሀብቱ ያለበትን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በአንዳች ምትሀታዊ ኃይል ብን ብሎ የሚያጠፋ ይመስል አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የሕዝብ ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን ያሳዩት ፈንጠዝያና እልልታ የሚያስተዛዝብ ነው” ብሏል፡፡

መግለጫው አክሎም ይህን ከፍተኛ የዋጋ ንረት የሚያስከትል የፖሊሲ ማሻሻያ “እንኳን ደስ አላችሁ” በሚል አጅቦ ለህዝብ ማስተላለፍ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለህዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳየበት ነው ሲል አበክሯል::

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የዶላር ዋጋ እየጨመረ ሲሆን በአንጻሩ የብር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል::

የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ዓለምአቀፍ አበዳሪ ተቋማት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን የፈቀዱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብድር ስምምነቶቹን ማጽደቁ ይታወሳል::አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button