ርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕሰ አንቀጽ፡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተፈጸም ያለው የድሮን ጥቃት የንጹሃን ዜጎች ሞት እያደረስ ይገኛል፤ መካላከያ ሠራዊት ሊቆጠብ ይገባል!

አዲስ አበባ፣ ጥር 3/2016 ዓ/ም፡_ በተለምዶ ድሮን በመባል የሚታውቁት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ ለውጊያ ዓላማዎች ጥቀም ላይ መዋል የጀመሩት በህዳር ወር 2013 የትግራይ ጦርነት ከተጀመረበት ገዜ ጀምሮ ነው። ለሁለት አመታት በዘለቀው ጦርነት በመንግስት በተፈጸመ የአየር ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ንሁሃን ዜጎች ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል። 

ታህሳስ 29 ቀን 2014 በሰሜን ምዕራብ የትግራይ ክልል በዴዴቢት በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን በያዘው የትምህርት ቤት ግቢ ላይ በተፈጸመው እጅግ አስከፊ የድሮን ጥቃት፤ በካምፑ ውስጥ የተጠለሉ ከ55 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ይህ ጥቃት ሰራዊቱ በሰዎች ላይ እየወሰደ ያለው የአየር ጥቃት እየጨመረ መሄዱን ከሚያሳዩ ምሳሌዎች አንዱ ነው።

በትግራይ ተጀምሮ አጎራባች ወደሆኑት አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተቋጨ በኋላ፤ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ የግጭት ስፍራዎች ላይ የመንግስት ኃይሎች ድሮኖችን ማሰማራታቸውን እንደቀጠሉና በርካታ የሰላማዊ ሰዎች ሞት እያስከተለ መሆኑን በርካታ ዘገባዎች አመልክተዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቅርቡ ባደረጉት ቃል መጠይቅ፤ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር በሚደረገው ውጊያ ድሮንን እንደሚጠቀሙ አስረድተዋል። “በአንድ አካባቢ የተሰበሰቡ ጽንፈኛ ተዋጊዎችን ካገኘን በደሮን እናጠቃቸዋለን” በማለት ድሮኖቹ የተገዙት ለመጠቀም መሆኑን ገልጸዋል። 

ይሁን እንጂ ፊልድ ማርሻሉ ሰላማዊ ሰዎች በድሮኑ ኢላማ አለመደረጋቸውን ተናግረዋል። “ የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት መጥፋትን ለማስቀረት ህዝብ ላይ ድሮን አንተኩስም” ሲሉ የተናገሩት ኢታማዦር ሹሙ እንዳንድ በኢላማ ተለይተው ነገር ግን የሰላማዊ ሰዎች ህይወት ለማትረፍ ሲባል ድሮን ላለምጠቀም የወሰነበት አጋጣሚዎች መሆራቸውንም ገልጸዋል። ነገር ገን መሬት ላይ ያለው እውነታ ከዚህ የተለየ ነው። 

ከሁለት ሳምንታት በፊት ሆሮ ጉዱሩ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ በሮ ቀበሌ በሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ወስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰላማዊ ሰዎች ሲሞቱ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ/ም የበሮ ሙሉውንጌል ቤተ ክርስቲያን አማኞችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያኗ አባሎች በቤተክርስቲያኗ ቀጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የበቆሎ ምርትን ለመሰብሰብ ላይ እያሉ የደሮን ጥቃቱ መፈጸሙን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። 

ካዛ ቀደም ብሎ በጥር ወር ውስጥ በሌላ አየር ጥቃት 12 ሰዎች መሞታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ጥቃቱ የተፈጸመው የኢሬቻ በዓል በተከበረበት መስከረም 26 እና 27 በተመሳሳይ ዞን ሃባቦ ጉዱሩ እና ኮምቦልቻ ወረዳዎች ላይ ነው።  ከአንድ አመት በፊት ጥቅምት 2015 ዓ/ም፤ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ጮቢ እና ሜታ ወልቂጤ ወረዳዎች ላይ መንግስት በወሰደው የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

መከላከያ ሰራዊት ከፋኖ ታጣቂ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ባለበት አማራ ከልል በተደጋጋሚ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶት የንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት እና አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ለማቶች ውድመት አስከትሏል። ህዳር 25 ወር 2016 ዓ/ም አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁስ የጫነ አምቡላንስ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አምስት ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው አንደኛው ክስተት ነው። በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ወገልጤና ከተማ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት አምቡላንስ ተሽከርካሪውን አወድሟል። 

በህዳር ወር  በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መነሃሪያ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁም አይዘነጋም። የተባሩት መንግስታት ድርጅት፣ የፋኖ ታጣቂዎች በዋቤር ከተማ የአውቶቡስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸማቸው እና የአየር ጥቃቱ ከመፈጸሙ ቀደም በሎ በዋዴራ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት በፋኖ ታጣቂዎች መያዙን አመላክቷል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ነሃሴ 2015 ዓ/ም በተፈጸመ ሌላ የደሮን ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ55 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በከተማው በሚገኘው ፍኖተሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፤ ሁሉም ተጎጂዎቹ ወንዶች መሆናቸውን እና ከአንድ የ 15 አመት ታዳጊ በስተቀር እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ እንደሆነ አስታውቋል። አንዳንድ ዘገባዎች በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች እስከ 70 እንደሚደርሱ ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥቅምት 2016 ዓ/ም ባወጣው ሪፖረት በደብረ ማርቆስ ከተማ ስምንት ንጹሃን ዜጎች የተገደሉበትን ጥቃት ጨምሮ በርካት የአየር ጥቃቶች  ንጹሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን አስታውቋል። 

ይህ በጦርነት ወቅት መንግስታት ለንጹሃን ዜጎች ጥበቃ እንዲያደርጉ የሚያስገድደውን ዓለም አቀፍ ህጎች በመጣስ መንግስት በጦርነት በተጎዱ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ላይ የሚፈጽመው የድሮን ጥቃቶች በሲቪሎች ላይ አስከፊ ተፅእኖ እያደረሰ ስለመሆን ማስረጃ ነው። ከሁሉም በላይ አሳሳቢ የሆነው ነገር መንግስት በድሮን ጥቃት ህይወታቸውን ላጡና ያለ ፍትህ ለቀሩ ተጎጂዎች ያሳየው ቸልተኝነት ነው። 

ምንም እንኳን ዒላማዎቹ የጠላት ተዋጊ ኃይሎች ላይ ቢሆኑም፣ በሰዎች ላይ ድሮን ማሰማራት፣ የስህተት አድሎች፣ የተጠያቂነት ጉድለት እና የህግ ማዕቀፈን አለመከተል የሚያሰከትል በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ እጅግ አደገኛ ወታደራዊ ዘመቻ ተደረጎ ይወሰዳል። በተዋጊዎች እና በሲቪል ቀጠናዎች ላይ በተሳሳተ የደሮን ኢላማዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ንጹሃን ዜጎች ሰለመሞታቸው የዓለም ህዝብ የሚያውቀው ነው። 

በመሆኑም፤ የመንግስት ኃይሎች በሰዎች ላይ ድሮን በመጠቀም ላይ ከፍተኛ መቆጠብ በማድረግ፣ ከመጠን በላይ ጥቅም ላይ የዋሉ የደሮን ጥቃቶች ያሰከተሉትን የሲቪሎችን ሞት በመመርመር ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ በመክፈል እና የድሮን ኦፕሬተሮችን ተጠያቂ በማድረግ ፍትህን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button