ዜናፖለቲካ

ዜና: በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተለመደ የመጣው ሰዎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ በትግራይ ክልልም እየተበራከተ ይገኛል - ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል ሰዎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እየተበራከተ ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)  ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳሰበ።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰዎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ነው ሲል የገለጸው ኢሰመጉ ከዚህ በፊት ከነበሩ አካባዎች በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእገታ ድርጊቶች እየተበራከቱ ይገኛሉ ብሏል፡፡

በማሳያነት በክልሉ በሃለቃ ኣከቦም መሓሪ አና ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ላይ የተፈጸሙ እገታዎችን የጠቀሰው መግለጫው አጋቾች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየጠየቁና ታጋቾችን በማንገላታት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የሚፈጸሙ የእገታ ድርጊቶችን እንዲያስቆም እና የሰዎችን የአካል ነጻነት እንዲያስከበር ጠይቋል።

መግለጫው በሌላ በኩል ከደቡብ አትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አካባቢ ለሚከናወን የደን ምንጣሮ በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ በፋኖ ታጣቂ ቡድን የተያዙ የቀን ሠራተኞች ከ25 ቀናት በኋላ መለቀቃቸው ቢገለጽም አሁን ያልተለቀቁ መኖራቸውን አስታውቋል።

“በዞኑ አስተዳደር ታግተው ጠፍተዋል ከተባሉት ሰዎች መካከል ያልተለቀቁ ሰዎች መኖራቸውን ካሰባሰብኳቸው መረጃዎች ተረድቻለሁ ያለው ኢሰመጉ የተወሰኑ ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደሚገኙ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጿል። የታገቱትና አሁንም ያሉበት ያልታወቁ ሰዎችን መንግስት በማፈላለግ ነጻ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ኢሰመጉ በመግለጫው በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የነበረውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ በትግራይ በእስር ላይ ከነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ200 በላይ ቢለቀቁም አሁንም በክልሉ በእስር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖራቸውን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በእስር ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን፤ የምግብ፣ የመጠጥ ውሀ እና የልዩ ልዩ መሰረታዊ አቅርቦቶች እጥረት እንዳለ በመጠቆም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአስቸኳይ የሚፈቱበትን ሁኔታ በማመቻቸት የአካል ነጻነት መብት እንዲያከብር ሲል ጠይቋል።

ኢሰመጉ በመግለጫው ካካተታቸው ጉዳዮች መካከል በአዲስ አበባ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያየዘ በመካሄድ ላይ ያለው የቤት ፈረሳ ይገኝበታል። በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ የፈረሳ እንቅስቃሴዎች ቤት እና ንግድ ቦታ ለሚፈርስባቸው ሰዎች ተገቢውን ጊዜ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡ ጠይቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button