ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በአማራ ክልል “የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ግድያ እየፈጸሙ በመሆኑ ከሰላም ማስከበር ተግባር ሊታገዱ ይገባዋል” - ሂዩማን ራይት ዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፡- አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ተቋም ሂዩማን ራይት ዎች ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል” ሲል ከሷል።

በመርአዊ የተፈጸመውን ግድያ በማሳያነት አቅርቧል። የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ከፋኖ ሀይሎች ጋር በሚያካሂዱት ውጊያ ንጹሃን ተገድለዋል ሲል ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል የተፈጸመውን የንጹሃን ግድያ በተመለከተ ገለልተኛ ምርመራ እንዲያካሂድ ተቋሙ ጠይቋል።

የመንግስታቱ ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት “የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎችን በሰላም ማስከበር ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ከማድረግ ለግዜው መቆጠብን አማራጭ እንዲያደርጉ” ሲል አሳስቧል።

ግፉ እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡ ከፍተኛ ሃለፊዎች ተጠያቂ እስኪሆኑ ድረስ የሀገሪቱ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተግባር ሊታገዱ ይገባል ብሏል።

የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት በአማራ ክልል በንጹሃን ላይ እየፈጸሙት ያለው አሰቃቂ ግድያ የሀገሪቱ መንግስት በአማራ ክልል ህግ ለማስፈን እየሰራሁ ነው የሚለውን ምክንያት የሚያጠለሽ ነው ሲል የተቋሙ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ለተሽያ ባድር መናገራቸውን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በአማራ ክልል የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት አባላት እየፈጸሙት ያለውን ግድያ እንዲመረምር መንግስታት በተለይም አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ዩኬ ግፊት ሊያደርጉ ይገባል ሲል አሳስቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ መንግስተ ንጹሃንን የገደሉትን የፌደራልም ሆነ የክልል የጸጥታ ሀይሎች ትርጉም ባለው መልኩ ተጠያቂ አለማድረጉ በሀገሪቱ የሚፈጸመው ግድያው እና ማሰቃየቱ እንዲቀጥል አስችሏል ሲል ገልጿል።

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ግጭት ባለባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ሆን ብሎ ንጹሃንን መግደል የየዕለት ስራቸው አድርገውታል ሲሉ የሂዩማን ራይት ዎች የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊዋ ለተሽያ ባድር መግለጻቸውን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button