ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና: “በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ አሳስቦኛል” - ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም፡- በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች ወሰን አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊቆም የገባል፣ ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲል ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰበ።

በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በአዲስ መልክ ግጭት መቀስቀሱን የጠቆመው ኮሚሽኑ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በአዋሳኝ አከባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችም መፈናቀላቸውን አመላክቷል።

ኮሚሽኑ ሁኔታውን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቆ ከሁለት ወራት በፊት በሁለቱ ክልሎች መካከል ተደርሶ የነበረው የሰላም ስምምነት መጣሱ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል።

በግጭቱ ሳቢያ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በግለሰቦች እና የህዝብ ንብረቶች ላይ ውድመት መከሰቱን የተመለከቱ መረጃዎች እንደደረሱት የጠቆመው ኮሚሽኑ በግጭቱ ሳቢያ በአከባቢዎቹ የደረሰው ጉዳት ግጭቶቹን እያባባሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ክልሎቹ በየግዜው የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለማርገብ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያደንቅ የጠቀሰው ኮሚሽኑ በቅርቡ በኢትዮጵያ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት በተደረገ ውይይት ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም ስምምነት መደረሱን አውስቷል።

ግጭቶቹን ለማስቀረት በፌዴራል እና በክልል ባለስልጣናት የተወሰዱ ላሉ እርምጃዎች እውቅና የሰጠው ኮሚሽኑ ቀጣይ ርምጃዎችን ለመከላከል ተጨማሪ ትኩረት ይሰጥ ሲል አሳስቧል።

ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የሁለቱ ክልል ባለስልጣናት ፍቃደኝነት የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጠይቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም ተፋላሚዎች በኢድ አል አድሃ በዓል መንፈስ ተግባብተው ውጊያው እንዳይባባስ እና ንጹሀን እንዳይጎዱ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽሯ አክለውም “በአካባቢው የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል በኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል መንፈስ እንዲከላከሉ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል” ብለዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button