ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኢትዮጵያ ከ500 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት 1 ሚሊየን ዩሮ መደበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5/ 2016 ዓ/ም፦ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚውል የ1 ሚሊዮን ዩሮ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ መመደቡን አስታወቋል። 

በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ከሓምሌ 2022 ጀመሮ 44,044 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን እና 571 ሰዎች መሞታቸውን ህብረቱ ገልጿል። 

ከመጋቢት 2023 ጀምሮ በኢትዮጵያ በፍጥነት እየተስፋፋ ያለው የኮሌራ ወረርሽኝ ከ2,276 በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ፤ 50 ሰዎችን ለህልፈት ህይወት ዳርጓል። 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሆነዋል

በግንቦት 2023 በወጣው ሪፖርት በ54 አካባቢዎች ወደ 6,200 የሚጠጉ ሰዎች ላይ በሽታው የታየ ሲሆን በዚህም ምክንያት 94 ሰዎች ሲሞቱ፤  7 ሚሊዮን ሰዎችን ለአደጋ አጋልጧል።  በነሀሴ ወር በኦሮሚያ፣ በሲዳማ እና በሶማሌ ክልሎች ከ16,800 በላይ ሰዎች በኮሌራ የተያዙ ሲሆን ከ370 በላይ ሰዎችም ሞተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በየካቲት ወር የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በአፋር፣ አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች 17 የኮሌራ ህክምና ማዕከላትን በኢትዮጵያ አቋቁሟል

ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በ9 ክልሎች  በየሳምንቱ ከ600 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የአውሮፓ ህብረት ገልጿል። “ድርቅ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ፤ ለወረርሽኙ የሚደረገውን ምላሽ እያደናቀፈ ሲሆን በዚህም ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው መያዝን እንደሚያስከትል ይጠበቃል” ተብሏል። 

የአውሮፓ ህብረት የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፉ፤ የሰብአዊ አጋሮች ከውሃ፣ ከንፅህና አጠባበቅ እና ከጤና ጋር የተያያዙ ፍላጎቶችን ለመደገፍ የሚውል ስሆን በተመረጡ አካባቢዎችም የኮሌራ ምላሽ ማስተባበሪያን ለማጠናከር እንዲሚረዳም ተገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአውሮፓ ህብረት ቀደም ሲል ህዳር 2023 በኢትዮጵያ ለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ1 ሚሊየን ዩሮ  አስቸኳይ ዕርዳታ መድቦ ነበር።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button