ማህበራዊ ጉዳይዋና ትረካ
በመታየት ላይ ያለ

ትረካ: ዕይታን መመለስ፤ በኢትዮጵያ የኮርኒያ ዓይነ ስውርነት ላይ የሚደረገው ትግል

በሞላ ምትኩ @MollaAyenew

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16/ 2016 ዓ/ም፦ በመላው ኢትዮጵያ በኮርኒያ ህመም የሚከሰት ዓይነ ስውርነት (Corneal Blindness) በመስፋፋት በርካታ ግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን እያዳረስ ይገኛል። ይህ አስከፊ ህመም ዕይታን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለው፣ ነፃነትንና እድሎችን ማሳጣት እንዲሁም ሰዎች ከማህበረሰባቸው ጋር የሚያስተሳስራቸውን ወሳኝ ግንኙነቶችም ያቋርጣል። የቅርብ ጊዜ ብሔራዊ መረጃዎች ባለመኖራቸው ምክንያት ትክክለኛ ቁጥሩን በግልጽ ማወቅ ባይቻልም፣ በባለሙያዎች ግምት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ አስከፊ በሽታ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

የኮርኒያ ዓይነ ስውርነት ተፅዕኖ ከግለሰቦች ሕይወት ባሻገር የሚንፀባረቅ ሲሆን ማህበራዊ መገለል፣ ኢኮኖሚያዊ ችግር እና የስነልቦና ጭንቀት የሚፈጥር ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮርኒያ ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሙሉጌታ ደሚሴ፣ ይህንን በሽታ ለመከላከል ትክክለኛ መረጃ አስፈላጊ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል። “የኮርኒያ ዓይነ ስውርነት ምን ያህል እንደተስፋፋ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ከሌለ ውጤታማ ሕክምናዎችን ማካሄድም ሆነ ሀብትን በበቂ ሁኔታ መመደብ አይቻልም” በማለት ሙሉጌታ ያብራራሉ።.

ምንም እንኳ እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች፣ የህመሙ ተጠቂዎች የዓይን ብርሃናቸውን መልሰው እንዲያገኙ ለማድረግ ያለድካም በቁርጠኝነት የተቻላቸውን ጥረት ሲያደርጉ በመቆየታቸው የተስፋ ጭላንጭል እየታየ ይገኛል። እንደ ሙሉጌታ ገለፃ፤ የኢትዮጵያ አይን ባንክ ከሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ከ2006 እስከ 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ2,177 በላይ የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ስራዎችን አከናውኗል። እነዚህ አመርቂ ውጤቶች፣ የዓይንን ብርሃን ብቻ ሳይሆን የጠፉ ህልሞችን ጭምር የመለሱ ሲሆን በተጨማሪም ግለሰቦቹ በዙሪያቸው ካለው ዓለም ጋር ዳግም እንዲገናኙ አስችሏቸዋል።

የኮርኒያ ዓይነ ስውርነትን ለመከላከል እነዚህ ጥረቶች ቢደረጉም፤ አንድ አሳዛኝ እውነታ ግን አሁንም አለ፤ የኮርኒያ ዓይነ ስውርነትን ለመዋጋት ከሚያስፈልገው ኮርኒያ፣ አቅርቦቱ እጅግ ያነሰ ነው። በዓይን ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ሲስተር ሊያ ቲካቦ፣ “ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከ 3,200 በላይ ኮርኒያዎችን ሰብስበን አከፋፍለናል፤ በየአመቱ ከ 200 እስከ 300 የሚደርሱ ኮርኒያዎችን እናሰራጫለን። ይሁን እንጂ ሂደቱ ከፍተኛ ገንዘብ የሚፈልግ በመሆኑ ክፍተቱ በጣም ሰፊ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ልዩነት እንደ ታሪኩ ሁሴን ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች፣ ዓለምን በዓይናቸው የማየት እድሉን ለማግኘት እንዲናፍቁ አድርጓል።  ታሪኩ ደስታ የሞላበት የልጅነት ጊዜው በድንገት ጨለማ ውስጥ የገባው ገና በሰባት ዓመቱ ነው። የዓይን ብርሃኑን ማጣቱ በማያውቀው አለም ውስጥ ከቶታል። 

ሆኖም፣ በዚያ ተስፋ መቁረጥ መካከል፣ ታሪኩ ጥንካሬን አገኘ። ለጨለማ መሸነፍን እምቢ በማለት የአይበገሬነት መንፈሱ ብርሃኑ ሆነ። ይህም የወደፊቱን መንገድ በማብራት እና ያጋጠሙትን ግዙፍ ፈተናዎች እና መገለልን እንዲያሸንፍ ኃይል ሰጥቶታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ዛሬ ላይ ታሪኩ፣ ሰዎች ምን ያህል ጠንካራ ሊሆኑ እንደሚችሉ አሳይቷል። ተግዳሮቶችን አሸንፎ የራሱን ልዩ የሕይወት ጎዳና አበጅቷል። አሁን የቴክኒሻንነት ሙያው በውስጡ ያለውን የማይናወጥ መንፈስ ያስተጋባል፤ ይህም በመከራ ላይ ድል ለመቀዳጀቱ ማረጋገጫ ነው። ታሪኩ “ተመሳሳይ ፈተናዎች ካጋጠሟቸው ጋር በመሆን፣ አሁን ከጨለማው ጉዞዎች ያገኘውትን ጥበብ፣ ሌሎች በራሳቸው መንገድ ወደ ብርሃን እንዲያመሩ አካፍላቸዋለው” ይላል። 

በተመሳሳይ የወጋየሁ ፈጠነ ታሪክ የማይናውጥ የጥንካሬ መንፈስን ያሳያል። ገና በአራት አመቱ በኮርኒያ ዓይነስውርነት መጠቃቱ በምርመራ ሲርጋገጥ ህይውቱ በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀየረ። ለአመታት በጨለማ ውስጥ በመኖሩ የአለምን ደማቅ ውበት ማየት ተስኖት ቆይቷል።  

ነገር ግን በ2008 የተስፋ ጭላንጭል ጨለማውን ስንጥቆ ወጣ። የተደረገለት ህይወት ቀያሪ የኮርኒያ ንቅለ ተከላ የአንድ ዓይኑን ብርሃን መለሰለት። ይህም የወጋየሁን የመኖር ፍላጎትን እንደገና አነቃቃ። “ይህ ውድ ስጦታ እውቀት የማግኘት ፍላጐትና ማንኛውንም ዕንቅፋት ለመቋቋም የሚያስችል ጽኑ ቁርጠኝነት አሳድሮብኛል” ብሏል ወጋየሁ።

በ2014 ሁለተኛው ነቅሎ ተከላ ባይሳካም የወጋየሁ የመንፈስ ጥንካሬ አልዋዥቀም። በጨለማ ውስጥ ለመኖር ፈቃደኛ ያልሆነው ወጋየሁ ትምህርቱን ለመከታተል በመምረጥ ለሌሎች መንገድ ማሳየት ችሏል።

የህክምና ባለሙያዋ ኤደን ተፈሪ (ዶ/ር) የኮርኒያ ዓይነ ስውርነት ደረሶባት ታውቃለች። ከኬራቶኮነስ ህመም ጋር ያደረገችውን ትግል ስታስታውስ ለለጋሿ እና የቀዶ ጥገና ሐኪሟ ያላትን ምስጋና ትናገራለች። ህይወቷን በመቀየር ረገድ ንቅለ ተከላው ምን ያህል ለውጥ እንዳመጣም ገልጻለች። 

የኤደን፣ ታሪኩ እና የወጋየሁ እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሌሎች ሰዎች ታሪክ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የጥንካሬ አቅምና ተስፋ እንዳላቸው የሚያሳይ ምስክር ነው። ታሪካቸው ተመሳሳይ ችግሮች ያጋጠሟቸውን ሰዎች እንድንደግፍ እና የአይን ብርሃን ለሁሉም ሰው እውን የሚሆንበት ዓለም እንዲኖር እንድንታገል ያሳስበናል። 

እነዚህ ግለሰቦች ከሌሎች ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን፣ የራሳቸውን መንገድ ካበራላቸው አስደናቂ የጥንካሬ መንፈሳቸው በመነሳት፣  የማይታላፉ የሚመስሉ መሰናክሎች ለሚያጋጥሟቸው ሰዎች የተስፋ ብርሃን ሆኖ የሚያገለግል ማህበር አቋቁመዋል። በማይናወጥ ቁርጠኝነታቸው እና ያለድካም በሚያደርጉት ድጋፍ፤ የብርታት መንፈስ ጨለማን የሚያሸንፍበት የወደፊት መንገድ እየጠረጉ ነው።

ታሪኮቸው፣ “የኢትዮጵያ ኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማህበር”ን መመስረት አስችሏል። የእነሱ ተሞክሮ ከተመሰረተው ድርጅት ጋር የተቆራኘ ነው ሲሆን  ይህ ድርጅት ሰዎች በጋራ ሲሰሩ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ምስክር ነው። የኢትዮጵያ ኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማህበር ከህክምና አግልጎሎት ባሻገር በኮርኒያ ዓይነ ስውርነት ለተጠቁ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ፣ የመመሪያ እና ተግባራዊ ድጋፍ ይሰጣል። ይህ ወሳኝ ድጋፍ ግለሰቦች ውስብስብ የጤና ስርዓቱን ለማለፍ እና የማህበረሰብ አባልነት ስሜትን በማዳበር ህይወታቸውን መልሰው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

ተጽዕኖዎቹ

በኢትዮጵያ ይህ አስከፊ ሁኔታ ስፍር ቁጥር በሌለው ሰዎች ሕይወት ላይ ረዥም ጨለማ ያስከትላል፤ የዓይን ብርሃን ብቻ ሳይሆን ተስፋ እና ዕድልንም ጭምር ያጠፋል። በገንዘብ፣ በግንዛቤ እጥረትና ብቁ የሆኑ የዓይን ስፔሻሊስቶች እጥረት ምክንያት የኮርኒያ ዓይነ ስውርነት እየጨመረ በመሄድ ስዎች እንዲገለሉ፣ እንዲደናቀፉና ያላቸውን አቅም እንዲያጡ ያደረጋል። 

ይህ ህመም በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የዓይን ብርሃንን ማሳጣት፣ በንባብና የእለት ተለት ክንውን ላይ ተጽዕኖ ያስከትላል። በተጨማሪም በራስ የመወሰን አቅም በማሳጣት እና እራስን የመቻል አቅም በመቀነስ በሰዎች ላይ ጥገኛ ያደርጋል።

ግለሰቦቹ፣ በውጣ ውረድ ውስጥ ያሳላፉት የየራሳቸው ጉዞ፣ ለሰው ልጅ ዘላቂ የመንፈስ ጥንካሬ ምስክርነት ነው። እንደ የኢትዮጵያ ኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማህበር ያሉ ድርጅቶች ከህክምና አግልጎሎት ባሻገር በህመሙ ለተጠቁ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የሞራል ድጋፍ፣ የምክር እና ተግባራዊ ድጋፍ ያቀረባሉ።

መፍትሄዎቹ

እንደ ኤደን ገለጻ እነዚህን ፈተናዎች ለማሸነፍ ዘርፈ ብዙ አካሄድን ይጠይቃል። “የዓይን ባንክን በራስ የመወስን አቅምን በማጠናከር ደምቦችን ማቃለል ቀልጣፋ በሆነ መንገድ መስራት ያስችላል። ጠንካራ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አውታር ተደራሽነትን በማስፋት አስፈላጊ አቅርቦቶች፣ በጣም ለሚያስፈልጋቸው  አካላት እንዲድርስ ያስችላል” በልዋል ።  

በትምህርት እና በስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ኢንቨስት ማደርግ ብቁ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች መፍጠር ያስችላል። እናም በመጨረሻ፣ ገንዘብ ማሰባሰብ እና መመደብ የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ፣ የኮርኒያ ዓይነ ስውርነትን ለመዋጋት የሚያስፈልጉትን መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ማግኘት የሚያስችለውን የገንዘብ አቅም  እንዲኖረው ያደርጋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ሙሉጌታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እነዚህን ፈተናዎች በቀጥታ በመታገል ይህንን ጨለማ ወደ ተስፋ መለወጥ እንደምትችል ተናግረዋል። እይታን መመለስ፣ ሰዎችን ማብቃት እና ማህበረሰቦችን አንድ ላይ ማስተሳሰር እንችላለን። የኮርንያ አይነስውርነት መከላከል እይታን መመለስ ብቻ ሳይሆን የሰውን አቅም መመለስ እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሩህ ውደፊትን መገንባትም ጭምር ነው ይላሉ ሙሉጌታ።

እንደ ሙሉጌታ ገለጻ ከመንግስት አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የዓይን ባንክ፣ የተለገሱ ኮርኒያዎችን በአግባቡ መጠቀምን ለማረጋገጥ የቢሮክራሲያዊ መሰናክሎችን ማሰስ አለበት።

“የኮርኒያ ልገሳን ማበረታታት፣ ለበረካቶች የወደፊት ብርሃንን የሚያስገኝ ነው” የሚሉት ሙሉጌታ ሌላኛው መፍትሄ ደግሞ ባላሙያዎችን ማብዛት እና ክትምህር ተቋማት ጋር አጋርነተን በማሳደግ የዘርፉን ባላሙያዎች ማብቃት ይቻላል በለዋል። በተጨማሪም የገንዘብ ድጋፍ ማደረግ አስፋላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህን ወሳኝ ዘርፎች ማለትም ምርምርን፣ ተደራሽነትን፣ ደንብን፣ የህዝብ ግንዛቤን፣ የሰራተኞች እድገትን እና የገንዘብ መረጋጋትን በአንድ ላይ በማጣመር የኮርኒያ ዓይነ ስውርነትን በሙሉ አቅም መፍታት እንችላለን ብለዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button