ዜናቢዝነስ

ዜና: ንግድ ባንክ “በፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሀገራችንን ማጥቃት ሲፈለግ ግንባር ቀደም ኢላማ” እየሆንኩ ነው ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም. የደረሰውን የሲስተም ችግር ተከትሎ የተፈጠረውን የአገልግሎት ማቋረጥ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም “በተለያየ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሀገራችንን ማጥቃት ሲፈለግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግንባር ቀደም ኢላማ (Target) ሁኗል” ሲል ገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ የባንኩ የመረጃ ደህንነት ስራ አመራር “በሃገራችን ላሉ ለሁሉም የፋይናንስ እና ሌሎች ተቋማት እንደ ማሳያ የሚሆን ቁመና ያለው ነው” ሲል የገለጸው መግለጫው ከተለያዩ አለም አቀፍ አካባቢዎች በየቀኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶች ቢሞከርበትም በጠንካራ የሳይበር ጥቃት መከላከያ ቴክኖሎጂ እየመከትኩ ነው ብሏል።

ባሳለፍነው ሳምንት መጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት የተፈጠረው ችግር “አንድ የሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስሕተት በመፈጠሩ” ነው ሲል የውስጥ ችግር መሆኑን አመላክቷል። ችግሩ በማጋጠሙ ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቷል፣ የኦዲት ስራው ስላልተጠናቀቀ ዝርዝር ጉዳይ ለማቅረብ አልቻልንም ብሏል።

በባንካችን ላይ የደረሰው ጉዳት ከባንካችን አቅምና ኃብት አንፃር እጅግ በጣም አነስተኛ ሊባል የሚችል ነው፣ በባንካችን ላይ የሚያደርሰው የጎላ ተፅእኖ የለም ሲል አስተባብሏል። የባንካችን ደምበኞች ሂሳብ ጋር ምንም ግንኙነት ስለሌለው ደንበኞቻችን ኃሳብ እንዳይገባችሁ ሲል አሳስቧል።

ባንኩ በመግልጫው “እጅግ በጣም ያሳዘነን ነገ የሀገር ተረካቢ ይሆናሉ ብለን የምንጠብቃቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንጀሉ ዋና ተዋናይ ሆነው ማየታችን ነው” ብሏል።

በየአካባቢው ያሉ የዲስትሪክት ኃላፊዎች በየአካባቢው ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button