አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17/ 2016 ዓ/ም፦ በኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 20/ 2017 በኋላ ወደ አስመራ እንዳይበር ማገዱን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፡ “በኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ስልታዊና በተቀናጀ መንገድ የተጓዦች ሻንጣዎች ላይ ስርቆት መፈጸምና መዘግየት፣ ዘረፋና የበረራዎች ሰዓት መዘግየት እንዲሁም ካሳ አለመስጠት” እየተፈጸመ ነው ብሏል።
በተጨማሪም የበረራ ትኬት ዋጋ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሷል።
በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግሮቹ እንዲቀረፉ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግም ፌሬ ማፍራት ባለመቻሉ ወደ አስመራ የሚደረገውን በረራ ማገዱን መግለጫው ገልጿል።
በመሆኑም ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚደረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች መታገዳቸውን አስታውቋል።
አክሎም ወደ ኤርትራ ለሚደረግ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ቀድመው የበረራ ማስተካከያ እንዲያደርጉና ሌላ አማራጭ እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ለማግኘት ያደረኘው ሙከራ አልተሳካም።
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የተቋረጠው በረራ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስልጣን መያዛቸውን ተከትሎ ባደረጉት የሰላም ጥረት 2010 ዓ.ም. መጀመሩ ዳግም መጀመሩ ይታወቃል። አስ