ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች እንዲለቀቁ፤ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ ኢሰመኮ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር ተያይዞ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። 

ኮሚሽኑ፤ በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ሊነሱ እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች ሊመለሱ ይገባል ሲልም ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ አክሎ አሳስቧል።

ኢሰመኮ፤ ይህን ያለው በክልሉ በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሆነውና ለአራት ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት ማብቃቱን ተከትሎ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል የጠየቀው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው ከነበሩ እስረኞች መካከል አስራ ዘጠኙ “የተሃድሶ ስልጠና’’ ከወሰዱ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት መፈታታቸው መዘገቡን ነው።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸምን በተመለከተ ግንቦት 20/ 2016 ይፋ ባደረገው ሪፖርት በክልሉ በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢ መሆናቸውን አስታወቋል። 

እጅግ አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መካከል ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል ይገኙበታል ብሏል።

በሪፖርቱ ከተጠቀሱ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መካከልም በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን 11 የአብነት ተማሪዎች ግድያ ይገኝበታል ሲል ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በአዋሽ አርባ፣ በአዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፤ በአማራ ክልል በባሕር ዳር፣ ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻና ጎንደር በሚገኙ የኮማንድ ፖስቱ ማቆያ ስፍራዎች እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በርካቶች ለተራዘመና የዘፈቀደ እስራት መዳረጋቸውን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button