ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዕለታዊ ዜና፡ ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ታህሣሥ 9፣ 2016 ዓ.ም:- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚን እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትንም አጽድቋል።

መክር ቤቱ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፅ/ቤት ሀላፊ ሆነው እያገለገሉ የቆዩትን ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአበላጫ ድምፅ በውሳኔ ቁጥር 2/2016 ሆኖ አፅድቋል።

ከዚህ በተጨማሪም አቶ ጌትነት ታደሰ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾመዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ሆነው እንዲሾሙ ያቀረቡትን ጥያቄ አፅድቋል። 

ምክር ቤቱ አቶ ጌትነት ታደሰን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አድርጎ  በውሣኔ ቁጥር 3/2016  በሙሉ ድምፅ  የቀረበውን ሹመት አጽድቋል።

አቶ ጌትነት ታደሰ በሚዲያ ዘርፍ የካበተ ልምድና ብቃት ያላቸው  መሆናቸውን በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚንስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ካቀረቡት ግለ-ታሪክቸው መረዳት ተችሏል ተብሏል።

አቶ መሳፍንት ተፈራ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሶማቸው ተገልጿል። ምክር ቤቱ አቶ መስፍን ተፈራን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አድርጎ በውሣኔ ቁጥር 4/2016 በሙሉ ድምፅ የቀረበውን ሹመት አጽድቋል ሲል አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ወይዘሮ ምዕላተወርቅም ማን ናቸው?

ወይዘሮ ምዕላተወርቅም ሆኑ አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት አዲስ አይደሉም። ሁለቱም ዕጩዎች ቦርዱን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። ወይዘሮ ምዕላተወርቅ ለሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ምርቋ ሜላትወርቅ የሥራ ሕይወታቸው የሚጀምረው በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ነው። በኮሚሽኑ ከጀማሪ የሕግ ኦፊሰርነት እስከ ኦፕሬሽን ኃላፊነት ድረስ ሰርተዋል። የኒው ጀኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተባባሪ መሥራች የሆኑት ሜላትወርቅ የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ የሕግ ድርጅት አቋቁመው ነበር።

ወይዘሮ ምዕላተወርቅ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ከሰላም እና ደኅንነት ጥናቶች ተቋም (አይፒኤስኤስ) የማስተርስ ዲግሪያቸው ተቀብለዋል። በተጨማሪም ከአሜሪካው ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በሕዝብ አስተዳደር ሌላ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው።

የምርጫ ቦርድ ሰብሰባቢ ዕጩዋ በአካዳሚክ፣ በፖሊሲ እና በፐብሊክ ሴክትር ባለሙያነት፣ በሁለትዮሽ እና በዘርፈ ባለብዙወገን ስምምነቶች ተደራዳሪነት፣ በግልግል ዳኝነት አማካሪ በመሆን ሰፊ ልምድ እንዳላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

የምዕላተወርቅ የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ትኩረት ስቦ በቦርዱ ሰብሳቢነት የሚያሾማቸው ከሆነ ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት በመምራት ሦስተኛዋ ሴት ይሆናሉ። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button