ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረምኩትን ስምምነት ለማቀላጠፍ የሚረዱ እርምጃዎች እየወሰድኩ ነው ስትል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13/2016 ዓ.ም፡- ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ለማቀላጠፍ የሚረዱ እርምጃዎች እየተወሰደች እንድምትገኝ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ስምምነቱን ለማቀላጠፍ እና ወደ ተግባር ለመለወጥ ይረዳ ዘንድ የሶማሊላን ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዳቸውን የጠቆመው መግለጫው ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል የቴክኒክ ኮሚቴ፣ አለም አቀፍ የህግ ባለሞያዎች ቡድን እና ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድኖችን ማቋቋማቸውን ጠቅሷል። ሂደቱን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉም አመላክቷል።

መግለጫው በተጨማሪም በአዲስ አበባ በተካሄደው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፈው ሶማሊላንድ ልዑክ ከኢትዮጵያ ጋር በተደረሰው ስምምነት ዙሪያ ለበርካታ ሀገራት ባለስልጣናት እና ተወካዮች ገለጻ ማድረጉን እና ከሀገራቱ ባለስልጣናትም አወንታዊ ምላሽ ማግኘቱን ጠቁሟል።

አለም አቀፍ ህግን በተከተለ መልኩ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት መፈጸማችንን፣ ከሁለቱ ሀገራት አልፎ ለቀጠናው የሚተርፍ ስምምነት መሆኑንም አስገንዝበናል ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ከኢትዮጵያ ጋር ያደረግነው ስምምነት ከምናስበው በላይ ለሶማሊላንድ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን በሙሉ ልብ እናምንበታለን ያለው የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር መስሪያ ቤቱ መግለጫ ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመለወጥ በትክክለኛ አካሄድ ላይ እንገኛለን ብሏል።

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ የፈጸሙት ተግባር አሳዛኝ ነው ሲል ተችቷል።

“በሌላ ሀገር የጸጥታ አካላት የሚጠበቁት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ” በአዲስ አበባ ድፍረት የተሞላበት አሳፋሪ ተግባር ነው የፈጸሙት ያለው የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ አለምአቀፍ የዲፕሎማሲ አካሄድን ባለመከተላቸው ከህብረቱ እና ከአስተናጋጇ ሀገር የጸጥታ አካላት ጋር “አስጠሊታ ሁከት” ፈጥረዋል ሲል ኮንኗል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት የፈጸሙት ተግባር ቅቡል የሆነው የዲፕሎማሲ አካሄድ የጣሰ ነው ሲል የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ተችቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button