ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በሃዲያ ዞን በተቀሰቀስ የኩፍኝ በሽታ 22 ህጻናት መሞታቸት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/ 2016 ዓ/ም፦  በማዕከላዊ ኢትጵጵያ ክልል ሃዲያ ዞን በተቀሰቀስ የኩፍኝ በሽታ በ14 ቀናት ውስጥ 22 ህጻናት መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጭ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ። 

በሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የላብራቶሪ ባለሙያ የሆኑት ነጋ ደሳለኝ በዞኑ የተቀሰቀሰው የኩፍኝ በሽታ በመስፋፋት ላይ መሆኑን እና በሾኔ ከተማ ብቻ ከ80 በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። 

“በታካሚዎች ብዛት እና በአልጋ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለታማሚዎች በጊዜያዊ ድንኳኖች ውስጥ ህክምና መስጠት ጀምሯል” ሲሉም  ነጋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዞኑ በምስራቅ እና ምዕራብ ባድዋቾ እና ሲራሮ ባድዋቾ ወረዳዎች ከ200 በላይ ሰዎች በኩፍኝ በሽታ ተይዘው ህክምና ላይ መሆናቸውን ባለሙያው አክለው ተናግረዋል።

እንደ ነጋ ገለፃ፣ ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 12 ዓመት የሚሆኑ  ህጻናት ናቸው። “ላለፉት ሁለት ሳምንታት በየቀኑ አንድ ወይም ሁለት ህጻናት በበሽታው ህይወታቸው እያለፈ ነው” በለዋል። 

የቫይታሚን ኤ ክትባት አለመኖር ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽዖ ማደረጉን የህክምና ባለሙያው ገልጸዋል። በዞኑ የሚገኙ ሆስፒታሎች የመንግስት ሠራተኞች ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ባደረጉት ስራ የማቆም አድማ ተዘግተው የነበረ በመሆኑ የክትባት የመስጠት ተግባር ላይ ተጽዕኖ ፈጥሯል ብለዋል። 

የክልል እና የዞን ባለስልጣናት ጥረቶች እንዳለ ሆኖ የበሽታው አስከፊነት ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። የሆስፒታሉ ባለሙያ በሀዲያ ዞን የተከሰተውን የኩፍኝ በሽታ ስርጭት ለመግታት የጤና ሚኒስቴር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button