አዲስ አባባ፣ የካቲት 29/ 2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ፤ “በፋኖ ታጣቂዎች” ትላንት የካቲት 28/ 2016 ዓ/ም በሶስት ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መሞቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
ጥቃቱ ትላንት ጠዋት ከ11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ ጂሩ ዳዳ፣ ወሬን ጋብሮ እና ማንቀታ ዋሪዮ በሚባሉ ቀበሌዎች መፈጸሙን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።
ስሙ እንዲጠቀስ ያለፈለገ የማንቀታ ዋሪዮ ቀበሌ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፤ ራሳቸውን “የፋኖ ታጣቂ” ብለው የሚጠሩ አካላት ከሃሙስ ጠዋት ጀምሮ በቀበሌዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ፤ በርካቶች ቆስለዋል።
በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ሽታዬ ዱባለ የምትባል የ 11 አመት ህጻን በጥይት ተመታ መገደሏን የገለጸው ነዋሪው፤ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን አክሎ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።
ማንቀታ ዋሪዮ በሚባለው ቀበሌ ውስጥ እስካሁን ጥቃቱ መቀሉን ነዋሪው ተናግሯል።
የወሬን ገርቦ ነዋሪ በበኩሉ በቀበሌው በተፈጸመው ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን፣ ንብረት መውደሙን እና ታግተው የተወሰዱ ሰዎች መኖራቸውን ገልጿል። ነዋሪው፤ “ሮጠው ማምለጥ የማይችሉ ህጻናት እና አረጋውያን አግተው ወስደዋል” ብሏል።
ጂሩ ደዳ በሚባለው ቀበሌ ”ከሃይማኖት ተቋማት ውጭ፤ የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ ከ400 በላይ ከብቶች ተወስደዋል። በርካታ መሰረተ ለማቶች ላይም ውድመት ደርሷል” ሲል ተናግሯል።
ነዋሪው አክሎም፤ በረካታ ሰዎች ህይወታቸውን ለማትረፍም፤ አቦቴ ወደሚባል በረሃ ተሰደዋል” ብሏል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ አያለውን ለማግኘት አዲስ ስታንዳርድ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። አስ