ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በሶማሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “የህይወት አደጋ ተጋርጦብናል” አሉ 

አዲስ አበባ፣ ጥር 25/2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ መንግስት ታህሳስ 11 የባህር በር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ በሶማሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ማስፈራሪያ እና ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። 

ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ የስምምነት ዜና መሰማቱን ተከትሎ “በኢትዮጵያ ዜጎች በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የህይወት አደጋ መደቀኑን” ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

“በጽሁፍ እየተላለፈ ባለው የማስጠንቀቂያ መልዕክት በሶማሊያ የምንኖር የኦሮሞ ተወላጆች ቀዬአችንን ለቀን እንድንወጣ ማስፈራሪያ እየደረሰን ነው” ብሏል።

እየተለጠፈ ያለው የማስጠንቀቂያ ጽሑፍ “በተወሰነው ግዜ ውስጥ ለቀህ የምትወጣ ከሆነ ህይወትህ፣ ንብረትህ እና በተሰቦችህ ይተርፋሉ፤ ነገር ግን ሳትወጣ ከቀረህ እየፎከሩ የምታያቸው ወጣቶች የህይወት ቀጣት የሚሰጡህ መሆኑን ቃል እንገባለን” የሚል መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ተመልክቷል። 

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረው ነዋሪ ጁባላንድ በሚባል አካባቢ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ላይ ግድያ መፈጸሙንና በሌሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል። አክሎም “የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግልን በደብዳቤ ብንጠይቀም እስካሁን ምንም የተደረገልን ጥበቃ ባለመኖሩ በታላቅ ፍርሃት ውስጥ ነን” ሲል ተናግሯል። 

ነዋሪነቱን ጁባላን በሚባል የአግሪቱ ክፍል ያደረገው ሌላኛው የኦሮሞ ተወላጅ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳረጋገጠው፤ የባህር በር ስምምነቱን ተከትሎ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው ተጽዕኖ እየከፋ ነው። 

“እየተካሄደ ያለው ማስፈራሪያ እና ማስጠንቀቂያ እጅግ አስጊ ነው፤ የተጠለፉ ስደተኞችም እንዳሉ እየሰማን ነው” ያለው የጁባላንድ ነዋሪው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽንን ጨምሮ የስደተኞች መብት ተሟጋች ለሆኑ ድርጅቶች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት መጠየቁን ተናግሯል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ አደጋ የተጋረጠው በሶማሊያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ በቻ ሳይሆን በሶማሊ ላንድ የሚገኙ ዜጎች ላይም ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል። ስምምነቱ ከተፈጸመ ሶስት ቀን በኋላ በሶማሊ ላንድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የአካል ጉዳት፣ የንብርት መዘረፍ እና የቤት ማቃጠል መኩራ እንደተደረገባቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። 

አዲስ ስታንዳርድ በሶማሊያ እና ሶማሊ ላንድ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጉዳይ በተመለከት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤትን በጽሑፍ አነጋግሯል። ጽ/ቤቱ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መልዕክት፤ በኢትዮጵያወያን ላይ እየተፈጸመ ነው ስለተባለው ጉዳይ ከስደተኞቹ ተወካዮች መረጃ እንደደረሰው በመግልጽ ነገር ግን “ጥቃት ተፈጸሞባቸዋል  ወደተባሉት አካባቢዎች መደረስ ባለምቻሉ መረጋገጥ አለቻልኩም” ሲል ገልጿል። 

ይሁን እንጂ ድርጅቱ ያለውን ስጋት ለብሔራዊ ስደተኞች ኤጀንሲ በማንሳት ስደተኞቹ ለአደጋ በተጋለጡበት አካባቢዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሠራተኞች አንዲሰማሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን ጠቅሷል። ከዚ በተጨማሪም ከመንግስት አካላት ጋር በመሆን የስደተኞቹን ድህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button