ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በሶስት ክልሎች መብራት የተቋረጠው የፋኖ ሀይሎች ባደረሱት ጥቃት ነው ሲል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27/2016 ዓ.ም፡- የአመራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የአማራ ክልል በርካታ ከተሞችን ጨምሮ በአመፋር እና በትግራይ የሚገኙ ከተሞች ከትላንት የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኤሌክትሪክ ሀይል የተቋረጠባቸው በፋኖ ታጣቂዎች በንፋስ መውጫ አካባቢ አንደኛው ፌዝ በመሳሪያ በመምታቱ ነው ብሏል።

“የካቲት 26/2016 ዓ/ም እኩለ ቀን አካባቢ ከባሕር ዳር – ደብረታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በንፋስ መውጫ አካባቢ አንደኛው ፌዝ በመሳሪያ በመምታቱ ከሠዓት በኋላ ጀምሮ አብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢ የመብራት አገልግሎት እንዲያጣ አድርጎታል።” ሲል ገልጿል።

የአማራ ክልል ህዝብ በቅጡ ያልተሟሉለት በርካታ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ችግሮች ባልተፈቱለት ወቅት እንዲህ አይነት ተግባር መፈጸሙን የኮነነው የፖሊስ መግለጫ የእለት ከእለት ህይወት በመብራት ላይ የተመሠረተውን ሕዝብ ወደ ሌላ የጨለማ ምዕራፍ ጎትቶ በማስገባት የስቃይ ዓይነቶችን እየፈለገ ሲተገብር መዋሉ የቀን ተቀን ተግባሩ ሆኗል ሲል ታጣቂ ቡድኑን ተችቷል።

“ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ባለፉት ግዜያት የተፈጠረውን ክፍተት አስቀድሞ ለመፍታት መንግሥት ለአርሶ አደሩ የሚልከውን ማዳበሪያ እንዳይደርስ ጉዞውን እያያስተጓጎለና እየዘረፈ ስለመሆኑ ሁሉም የሚያውቀው የእለት ተዕለት ተግብሩ ሆኗል” ሲል አውስቷል።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ በርካታ ከተሞች ኃይል መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል።

ከባህር_ዳር – በደብረታቦር – ንፋስ_መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአካባቢዎቹ ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት ዛሬ 26 ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በንፋስ መውጫ አካባቢ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ አንደኛው ፌዝ በመበጠሱ ከንፋስ መስጫ – ጋሸና- #ላማጣ – መሆኒ – መቀሌ የሚሄደው መስመር ኃይል ተቋርጣል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ መልኩ ከደብረ ብርሃን – ሸዋሮቢት – ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ከኮምቦልቻ በባቲ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል መዲና ሰመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የደረሰውን ጉዳቶች በአፋጣኝ በመጠገን አገልግሎቶቹን ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button