ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 የጉጂ ዞን ሚሊሻዎች ተገደሉ 

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/ 2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰርማሌ ወረዳ ቲፋቴ ቀበሌ ድንበር አካባቢ የታጠቁ ሀይሎች በፈጽሙት ጥቃት በጉጂ ዞን የተመደቡ 12  የሚሊሻ አባሎች መገደላቸውን እና ሁለት መቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና ኃላፊዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰርማሌ ወረዳ ቲፋቴ ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆኑት ሙሃምድ ኪታሞ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት መሆናቸው የተገመተ ታጣቂዎች ማክሰኞ ጥር 14 በፈጸሙት ድንገተኛ ጥቃት ሚሊሻዎቹ ተገድለዋል። 

ጉዳት የደረሰባቸው ሁላቱ ሚሊሻዎች በአቀራቢያ ወደሚገኘው ቀሌ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያ ገዛኀኝ አንዳሻ ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። 

የቲፋቴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ነቢዩ ነጋሽ፣ ታጣቂዎቹ ሚሊሻዎቹን ከገደሉ በኋላ መሳሪያቸውን ወስደው ተሰውረዋል ብለዋል።  

እንደ ነዋሪው ገለጻ በአካባቢው በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፍ ነው። አዲስ ስታንዳርድ ለተጨማሪ መረጃ የጉጂ ዞን ኃላፊዎችን ለማግኘት የደረገው ሙከራ አልተሳካም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button