ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በትግራይ የፌደራል መንግስት እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ባለመቻላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሀብ እየሞቱ ነው – ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21/2016 ዓ.ም፡- በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ከግምት በማስገባት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ እና የአለም የምግብ ፕሮግራም ለተጎጂዎች የሚያቀርቡትን እርዳታ እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጥር 21 ቀን ባወጣው መግለጫ ተማጸነ።

በትግራይ የፌደራል መንግስት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በቂ የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ባለመቻሉ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሀብ ምክንያት መሞታቸውን ባሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳት መቻሉን ኢሰመጉ አስታውቋል።

በትግራይ ክልል ያለው ረሀብ አሁንም ድረስ ተገቢ የሆነ መፍትሔ እና ምላሽ ባለማግኘቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ያለው የኢሰመጉ መግለጫ በዋናነት የአገር ውስጥ ተፈናቃይ የሆኑ ሴቶች፣ ጨቅላ ህጻናት፣ አጥቢ እናቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ከሟቾች ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸውን ገልጿል።

ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት የሆኑ እንደ የአሜሪካ ኤጀንሲ ለዓለም አቀፍ ልማት (USAID) እና የዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም (WFP) በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ያቋረጡትን የምግብ እና የመድሀኒት ድጋፍ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲያስጀምሩ ሲል ጠይቋል።

የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ ያለባቸውን ኃላፊነቶች እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰተው ድርቅ ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱና አሁንም ድረስ በክልሉ የቀጠለ ግጭት በመኖሩ ምክንያት በረሀብ በርካታ ሰዎች እና እንስሳት እየሞቱ ነው ያለው ኢሰመጉ  በአካባቢዎቹ ባለው ግጭትም ምክንያት በበቂ ሁኔታ ሰብዓዊ ድጋፍን ማቅረብ እንዳልተቻለ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል።

በአማራ ክልል በዋናነት በማዕከላዊ ጎንደር፣ በደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፣ በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ጃናሞራ እና ጠለምት አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ድርቅ መከሰቱን ከወራት በፊት በመግለጽ ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቡን አውስቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button