ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል ላይ የመከላከያ ሰራዊት ዘመቻ ያካሄደው በክልሉ የነበሩ እና ጥቃት የተፈጸመባቸውን ክፍለ ጦሮች ለማዳን ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም፡- የሀገር መካላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ዘመቻ ያካሄደው በዋናነት በክልሉ የነበሩ እና በጽንፈኛ ሀይሎች ጥቃት የተፈጸመባቸውን ክፍለ ጦሮች ለማዳን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈጸመው ተግባር ተሞክሮ የወሰዱ በሚመስል መልኩ በአመራ ክልል በነበሩ የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል ሲሉ ፊልድ ማርሻሉ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተደምጠዋል።

ጽንፈኛ ሀይሎች ሲሉ ፊልድ ማርሻሉ የጠሯቸው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች “የክልሉን መዋቅሩን በሙሉ ወረው ሰራዊታችንን መቱ” ብለዋል፤ “ትግራይ ላይ የተደረገው ተደገመ” ሲሉ ገልጸዋል።

የትግራይ “የገነነው አንድ ሙሉ እዝ የታጠቀ ሀይል እዚያ ስለነበረ ነው” ሲሉ የተደመጡት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ “አማራ ክልል ግን ትልቅ ሀይል አልነበረም፣ ነገር ግን ትግራይ ላይ እንደተደረገው በነዚህ ወታደሮች ላይ ተመሳሳይ ነገር ተደረገ” ብለዋል።

መንግስት የአማራ ክልልን በጣም ነው ያስታመመው ያሉት ብርሃኑ ጁላ በክልሉ ሲሰራ የነበረው ሴራ የምናውቀው ከትግራዩ ጦርነት በፊት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ቀድመን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ብለን ዝም ስላልን ነው፣ እውነት ቢኖርህም ህዝብ ይፈርድብሃላ ሲሉ የተደመጡት ፊልድ ማርሻሉ “እኛ ደግሞ ህዝብ እንዲፈርድብን አንፈልግም፤ ህዝብ በደንብ ተረድቶት እራሳችንን ለመከላከል መንቀሳቀስ ይሻላል” ብለን ድህረ ርምጃ ነው የወሰድነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ሁለተኛነት የመካላከያ ሰራዊቱ በአማራ ክልል ዘመቻ ያካሄደው “ይሄንን ሀይል ስርአት ለማስያዝ ያስፈልጋል ተብሎ” ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች መከላከያ ሀይሉ ባካሄዳቸው የድሮን ጥቃቶች ንጹሃንን እየገደለ ነው ተብለው የተጠየቁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ሕዝብን በድሮን መትተን አናውቅም። እኛ በጥናት ላይ የተመሠረተ ታጥቆ እና ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ፀረ ሰላም ኃይልን ለይተን እንጂ ሕዝብን በድሮን አንመታም” ሲሉ አስተባብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በጎረቤት ሶማሊያ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን በሰጡበት ክፍል ፊልድ ማርሻሉ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሶማሊያ ግዛት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚጠበቅ መሆኑን በመግለጽ የኢትዮጵያ ጦር ሙሉ በሙሉ ለቆ ቢወጣ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ሞቃዲሾ የሚቀመጥ አይመስለኝም ብለዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button