ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ3 ሺህ 225 ትምህርት ቤቶች ትምህርት አለመጀመሩን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር እየሠራ መኾኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ መኳንንት አደመ አስታወቁ። በክልሉ በፀጥታ ችግር ምክንያት በ3 ሺህ 225 ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርት አለመጀመሩንም ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከምዕራብ አማራ ዞኖች ትምህርት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የትምህርት ሥራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ አየተካሄደ እንደሚገኝ አሚኮ ዘግቧል።

መንግሥት አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ለማድረግ እየሠራ ነው ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል ያለው ዘገባው ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ማሳሰባቸውን አስታውቋል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት በ3 ሺህ 225 ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርት አለመጀመሩንም በንግግራቸው አንስተዋል ያለው ዘገባው በ2016 የትምህርት ዘመን በክልሉ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዶ እንደነበር ኀላፊው ገልጸዋል ብሏል፡፡

በክልሉ 10 ሺህ 813 ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ ሃላፊው ጠቁመዋል ያለው ዘገባው በ3 ሺህ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በ225 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርት እንዳልተጀመረ ገልጸዋል ብሏል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button