ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኢትዮጵያ የተከሰተው “ድርቅ እንጂ ርሀብ” አለመሆኑን በዓለም አቀፍ ተቋማት ጥናት እና በባለድርሻ አካላት ፈጣን ዳሰሳ ተረጋግጧል – ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም

አዲስ አበባ፣ ጥር 27/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚያ ለማዋል የሚደረግ ጥረት ተገቢ ያልሆነና በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ገለጹ።

በኢትዮጵያ የተከሰተው “ድርቅ እንጂ ርሀብ” አለመሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ በዓለም አቀፍ ተቋማት ጥናት እና በባለድርሻ አካላት ፈጣን ዳሰሳም ርሃብ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በመሆኑም የተከሰተውን “ድርቅ ለፖለቲካ” አላማ ማስፈፀሚ ለማዋል የሚደረግ ጥረት ተገቢ ያልሆነና በፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስረድተዋል ያለው ዘገባው ለተከሰተው “የድርቅ አደጋ” መንግስት አፋጣኝ ሰብአዊ ድጋፍና የተቀናጀ ምላሽ እየሰጠም ይገኛል ማለታቸውንም አስታውቋል።

እርዳታ ሰጭዎች ያለምንም ማስጠንቀቂያ ድጋፍ ባቆሙበት ወቅት መንግስት ተጨማሪ ሀብት በመመደብ ዜጎቹን መታደግ መቻሉን አስታውሰዋል ያለው ዘገባው በቀጣይም ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ማለታቸውን ጠቁሟል።

የሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት ባለፈው አንድ ዓመት ከግማሽ የድጋፍ ምላሻቸው የተቀዛቀዘ ስለነበር ከ70 በመቶው በላይ በመንግስት አቅም መሸፈኑን ገልጸዋል ያለው ዘገባው ከሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት አንጻር ባለፈው አመትም የተገኘው 33 በመቶ ብቻ መሆኑን አስታውሰው መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት በ 11 ቢሊዮን ብር ወጭ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል እህል ገዝቶ አከፋፍሏል ማለታቸውን አካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button