ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በክልሉ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 528 ታጣቂዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ሊቀላቀሉ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1/ 2016 ዓ/ም፡ በአማራ ክልል ጎንደር ቀጣና የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 528 ታጣቂዎች በቅርቡ የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ የሚቀላቀሉ መሆኑን ሰሜን ምዕራብ ኮማንድ ፖስት የጎንደር ቀጣና ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል ዋኘው አለሜ ገለጹ፡፡

በጎንደር ቀጣና እስካሁን 528 ታጣቂዎች ጥሪውን መቀበላቸውን ገልጸው፤ ከእነዚህ መካከልም 234 የሚሆኑት ከእነመሳሪያቸው የገቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሚኖሩባቸው ቀበሌ እና ወረዳዎች የወንጀል ሪከርድ እንደሌላቸው ተረጋግጦና የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው አካባቢያቸውን የሰላም ዘብ በመሆን እንዲጠብቁ ይደረጋል ነው የተባለው።

ከ528ቱ ታጣቂዎች መካከልም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን 119 የሚሆኑት የተሃድሶ ሥልጠና መውሰድ መጀመራቸውን ጠቁመው፤ ቀሪዎቹም በቅርቡ ሥልጠና እንዲጀምሩ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

እየተሰጣቸው ያለውን ሥልጠና በአግባቡ ተከታትለው በማጠናቀቅ በአካባቢያቸው የሰላም አምባሳደር እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠዳ ወረዳ የተሃድሶ ሥልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት ታጣቂዎች መንግሥት ላደረገላቸው የሰላም ጥሪ አመስግነው ሕዝባቸውን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘገቧል።

የሰሜን ምዕራብ ኮማንድ ፖስት የጎንደር ቀጣና ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል ዋኘው አለሜ፤ በተለያዩ ቅስቀሳዎች በመደናገር ወደ ጫካ የገቡ ታጣቂዎችን ኮማንድ ፖስቱ መስፈርቶችን በማውጣት በወዶገብነት እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከተመላሽ ታጣቂዎቹ ጋር በነበራቸው ውይይትም ሥልጠናው የነበሩ ስህተቶችን ተገንዝበው ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱና ሕብረተሰቡን ለማገልገል ያዘጋጃቸው መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።ሌላኛው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባል ሳዲቅ አደም፤ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በሥልጠና ላይ ያሉት ታጣቂዎች በሰላም ጉዳይ ላይ በቅንነት ለመሥራትና ሕብረተሰቡን ለማገልገል እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button