ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6/2016 .ም፡ በቅርቡ ከተቋቋሙት የሀገሪቱ ክልሎች አንዱ በሆነው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የአራት ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ። አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች እንዳስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል በተፈጠረ አስተዳደራዊ ልዩነት ግጭቱ መቀስቀሱን አመላክተዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የወልቂጤ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ አርብ እለት ሁለት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በከተማው ዳርቻ በቡድን የተደራጁ ሰዎች ያደረሱባቸውን ጥቃት ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱን ተናግረዋል።

ሁኔታው ተባብሶ በቀቤና ልዩ ወረዳ የሚገኙ እና የታጠቁ ቡድኖች በከተማዋ ዳርቻ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን እና በአከባቢው በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን፣ ዘረፋ መፈጸሙን እና ንብረት መውደሙን አስታውቀዋል።  

ነዋሪው ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጋር በተያያዘ የቆየ ውጥረት እንደነበር ጠቁመዋል። የውጥረቱ መነሻም አዲሱ ክልል ከመመስረቱ በፊትም የወልቂጤ ከተማ የቀቤና እና የጉራጌ ወረዳዎች አስተዳደራዊ ማዕከላዊነት ጋር የተያያዘ መሆኑን አመላክተዋል።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ የጸጥታ አስከባሪ ሀይል አባል ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በታጣቂው ቡድን እና ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ህይወቱ ማለፉን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።  በነገታው ጥቅምት 4 ቀን 2016 ላይ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በከተማዋ ዳርቻ በታጣቂ ቡድኑ በተፈጸመበት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቱን ማለፉንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ነዋሪው ሁለት የቀቤና ተወላጆች ቆላ ከባዳ በተባለች ቦታ በነበረው የተኩስ ልውውጡ ህይወታቸው ማለፉን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ከጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በከተማዋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ንብረት መውደሙን፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን አስታውቆ በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመሆኑም ከጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ መጣሉን አስታውቋል። በተጨማሪም ማነኛውም ተሽከርካሪ ማለትም ሞተር ዳይክል፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣ አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ከቀኑ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button