ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አሜሪካ በመርአዊ የተፈጸመው የንጹሃን ግድያ እጅግ እንዳሳሰባት ገለጸች፣ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራም ጠይቃለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በሰሜን ጎጃም ዞን በመርአዊ ከተማ በንጹሃን ላይ የተፈጸመው ግድያ እንዳሳሰበው በመግለጽ ሁኔታው በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የአሜሪካን መንግስት ጠየቀ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር በሆኑት ኤርቪን ማሲንጋ ባወጡት መግለጫ “ባልተገደበ ሁኔታ ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተቋማት ቦታውን እንዲጎበኙ እና ወንጀለኞችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ” ጠይቀዋል።

አምባሳደሩ በመግለጫቸው በኦሮምያ እና በአማራ ክልሎች በመንግስት እና በታጣቂ ሀይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ መሆኑን የሚያሳዩ አሳሳቢ የሆኑ ሪፖርቶች እየወጡ እንደሚገኙ በመጠቆም ብቸኛው መንገድ ድርድር ማካሄድ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

በመርአዊ ከተማ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለስድስት ሰዓታት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱን እና በዕለቱ “ጅምላ ጭፍጨፋ” በሚመስል መልኩ በንጹሃን ላይ በተፈጸመ ግድያ በትንሹ 50 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ባወጣው መግለጫ በመርዓዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 (ሰማንያ) በላይ የሆኑ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል። ከግድያው በተጨማሪ የአካል ጉዳት፣ ድበደባ፣ ማስፈራራትና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button