ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎችን መቀበሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2/2016 ዓ.ም፡- አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎች መቀበሉን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያስመረቅም መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 የትምህርት ዘመን የሚያስተምራቸውን አዲስ ተማሪዎች የተቀበለው የመመገቢያ፣ የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ለመማር ማስተማር ሥራው አስፈላጊ የሆኑ የዝግጅት ሥራዎችን ካጠናቀቀ በኋላ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ከበደ መግለጻቸውን ዘገባው አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠው ከነበሩ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከል ዳግም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1ሺህ 500 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ እንደሚያስመርቅም አቶ ዮሐንስ መናገራቸውን ጠቁሟል።

ተቋሙ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከ22 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች አሰልጥኖ ማስመረቁን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ዋቢ በማድረግ ዘገባው አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button