ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ “በተደራራቢ መርሀ ግብር” ምክንያት በነገው የኢጋድ ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 8/ 2016 ዓ/ም፡_ ኢትዮጵያ፤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግታት ድርጅት (ኢጋድ) በነገው ዕለት ጥር 8 ቀን 2016 ዓ/ም በሚያካሄደው ጉባዔ ላይ “በተደራራቢ መርሀ ግብር” ምክንያት መገኘት የማትችል መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል አሳወቀች። 

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር እና ለኢጋድ በላከው ድብዳቤ “ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘው መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ መሆኑ እና የተቀመጠው ጊዜ አጭር መሆኑ ” ኢትዮጵያ በኡጋንዳ ካምፕላ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብሏል።

ይሁን እንጂ “ኢትዮጵያ ኢጋድ በሚመራበት ደምብ መሰረት በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ ናት” ሲል ደብዳቤው አክሏል። ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ቅርብ የሆኑ ምንጭ ለአዲስ ስታንዳርድ በማህበራዊ ሚዲያ በመሰራጭት ላይ ያለውን የደብዳቤው ትክክለኝነት አረጋግጠዋል።

አዲስ ስታንዳርድ ከኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ እና በሱዳን እየተካሄደ ባለው ግጭት ዙሪያ ለመመከር ቀነ ቀጠሮ መያዙ ተገልጿል። የጁቡቲው ፐሬዝዳንትና የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት ኢስማዔል ጌሌ አባላቶቹ ጥር 9 በኡጋንዳ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቀረበዋል።

የሱዳን መንግስት በታቀደው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት – ኢጋድ ስብሰባ ላይ የማይሳተፍ መሆኑን ቀደም ብሎ አስታውቋል።  በተጨማሪም ከኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን አስታውቋል።

ከጁቡቲም ሆነ ከኢጋድ ኢትዮዮያ እና ሱዳን ስብሰባው ላይ አለመሳተፋቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ስብሰባዉ በታቀደው መሰረት የሚካሄድ ሰለመሆኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button