ዜናቢዝነስ

ዜና፡ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የላዳ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ መገጣጠም የሚያስችለው ስምምነት ከኩባንያው ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8/2016 .ም፡ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የላዳ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ መገጣጠም የሚያስችለውን የፍላጎት ሰነድ ስምምነት ከሩሲያው ላዳ ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ተገለጸ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሱሌማን ደደፎና የላዳ ኩባንያ የሽያጭና ገበያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሊያ ሳቪኖቭ መፈራረማቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውቋል።

የፍላጎት ስምምነቱ የላዳ ኩባንያ ምርት የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ መገጣጠም የሚያስችል ነው ሲሉ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ መናገራቸውን ያስታወቀው ዘገባው በዚህም በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ስምምነቱን ተግባራዊ እንደሚደረግም መግለጻቸውን ጠቁሟል።

ምርቶቹ በዋናነት ለአገር ውስጥ ገበያ የሚውሉ መሆናቸውን እና በሂደትም ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እንደሚቀርቡ መገለጹንም አካቷል።

የላዳ ኩባንያ የሽያጭና ገበያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሊያ ሳቪኖቭ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ጠንካራ ወዳጅነት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እድል መፍጠሩን ጠቁመውል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button