ዜናማህበራዊ ጉዳይቢዝነስ

ዜና፡ ዋሻ የተናደባቸው የኦፓል ማዕድን አውጭዎችን ለማትረፍ የሚደረገው ጥረት አራተኛ ቀኑን ቢያስቆጥርም ውጤት አልተገኘም ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4/2016 ዓ.ም፡- በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ “018 አለኋት” ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከሃያ በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩ ይታወቃል።

የተዳፈኑትን ወጣቶች ለማውጣት የቦታው አቀማመጥ ለማሽን የተመቸ ባለመሆኑ በሰው ኃይል በቁፋሮ ህይወታቸውን ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያጋራው መረጃ ያሳያል።

ዋሻው ከ750 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መሆኑን የጠቆመው የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ለዋሻው መግቢያ ቅርበት ባለው የውስጠኛው ክፍል ላይ በሚደረግ ጥረት የወጣቶቹን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣን እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር ሊቀመንበር እንደነገሩት ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ እንዳደረገባቸው ዘገባው አመላክቷል።

ስምንቱ የማኅበሩ አባላት በናዳው ተይዘው እንደሚገኙ ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ ነግረውኛል ያለው ቢቢሲ እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ ነው ማለታቸውንም አካቷል።

አደጋው ከተከሰተ በኋላ በመንግሥት በኩል የተቀበሩትን ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅም ሆነ ከዋሻው ለማውጣት የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለም መግለጻቸውንም አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button