ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርን ጨምሮ የሚኒስትሮችን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30/2016 ዓ/ም፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 30/ 2016 ዓ/ም ባካሄደው 15ኛው መደበኛ ስብሰባ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና የጤና ሚንስትር ሹመቶችን አጽድቋል። 

በዚህም መሰረት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። 

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመተካት የገዢው ብልጽና ፓርቲ ሁለተኛው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ህዳር 2011 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ውስጥ ስማቸው  በጉልህ ከሚጠቀስ ሰዎች ውስጥ አንዱ ሆነዋል። ለጠቅላይ ሚንስትሩም ቅርብ ታማኝ መሆናቸው ይታመናል። ነሃሴ 2015 ዓ/ም በአማራ ክልል የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ተመርጥዋል። 

ሰኔ 2011 ዓ.ም የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር አምባቸው መኮነን፣ ሌሎች የአዴፓ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ከተገደሉ አንድ ወር በኋላ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል። 

ከዚህ ቀደም ብሎ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደህንነት አማካሪ የነበሩ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለበርካታ አመታት አብረው ሰርተዋል። 

በዛሬው ዕለትም አቶ ተመስገን ለረጅም አመታት በጠቅላይ ሚንስትርነት ያገለገሉትን አቶ ደመቀ መኮንን በመተካት ተሾመዋል። አዲስ ስታንዳርድ አቶ ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር በተጨማሪም ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኃላፊነታቸው መሸኘታቸውን ዘግቧል

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከዚህ በተጨማሪም የጠቅላይ ሚንስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት የቀድሞው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም ዶ/ር ሊያ ታደሰን በመተካት የማህጸንና ጽንስ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።  ዶ/ር መቅደስ በስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ ዕቅድ ሰብስፔሻይዝ ያደረጉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው። 

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህፀን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ይህ ሹመት እስከተሰጠበት ድርስ የአለም ጤና ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት በቡድን መሪነት አገልግለዋል። የ2014 የፊጎ ሽልማት ተሸላሚ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።በተጨማሪም ትዕግስት ሃሚድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button