ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የመንግስት ባለስልጣናት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ለማፈን መጠቀማቸውን ሊያቆሙ ይገባል – አምነስቲ ኢንተርናሽናል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በሀገሪቱ በሰላማዊ መንገድ መንግስትን የሚቃወሙ፣ አጥብቀው የሚተቹ ታዋቂ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ለማሰር እየተጠቀመበት ይገኛል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መልለጫ አስታውቋል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መጽደቅ ባለፉት ስድስት ወራት የመንግስት ባለስልጣናት በመላ ሀገሪቱ በመንቀሳቀስ ተጠርጣሪዎችን ያለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ የማሰር፣ የሰዓት ገደብ መጣል፣ ወደ ማንኛውም ቦታ ያለገደብ የመንቀሳቀስ መብትን የመገደብ እና የመሰብሰብ መብትን መከልከል እንዳስቻላቸው ገልጿል።

“የኢትዮጵያ መንግስት እደቀድሞ ዘመኑ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሰበብ መሰረታዊ የሰበአዊ መብቶችን ለመገደቢያነት መጠቀሙን ሊያቆም ይገባል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ የየምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ማሳሰባቸውን አመላክቷል።

ሃላፊው በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በትጥቅ የታገዘ ግጭት፣ በትግራይ ክልል ከፈተኛ የሰብአዊ ቀውስ፣ በኦሮምያ አሳሳቢ የጸጥታ ችግር ተጋርጦባት ይገኛል ማለታቸውንም ባወጣው ሪፖርት አሳስቧል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መራዘም በሀገሪቱ የነጋሪት ጋዜጣ አልታተመመ ያለው አመነስቲ በመግለጫው ይህም ግልጽነት የጎደለው፣ መረጃ የማግኘት መብትን የጣሰ እና ህጋዊ መርህን ያልተከተለ ነው፤ ዜጎች የትኞቹ ተግባራት እና የት ቦታ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሊያስጠይቃቸው እንደሚችል መረጃ እንዳይኖራቸው አድርጓል ሲል ተችቷል።

አምስት ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች እና ሶስት ጋዜጠኞች ያለምንም ክስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ከቤተሰቦቻቸው መረዳት መቻሉን ጠቁሟል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መተግበር ከጀመረ ወዲህ በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል ሰዎች በገፍ እየታሰሩ ነው ብሏል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መተግበር ቢፈቅድላቸውም የመንግስት ባለስልጣናት ዜጎቹን በገፍ ማሰር ማቆም አለበት፣ የሀገሪቱን ህጎች እና አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ማክበር ይገባቸዋል፣ ከፍተኛ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን ጨምሮ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በገፍ የታሰሩ ክስ ሊመሰረትባቸው አልያም ሊለቀቁ ይገባል ሲል አሳስቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button