ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የክልሉ መንግስት ያስተላለፈውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ “ከ5 ሺህ በላይ ታጣቂዎች መመለሳቸውን” የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ነፍጥ አንስተው በመዋጋት ላይ ላሉ ታጣቂዎች ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ “ከ5 ሺህ በላይ ታጣቂዎች መመለሳቸውን” የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንገሻ ፈንታው በክልሉ “በአራቱም ቀጣናዎች 5 ሺህ 216 ታጣቂዎች ሰላምን በመምረጥ ወደ መቀበያ ማዕከላት” ገብተዋል ማለታቸውን ቢሮው በማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።

በቀጣይም በርካታ ታጣቂዎች እንደሚገቡ ይጠበቃል ያሉት ሃላፊው “የገቡት ታጣቂዎች አስፈላጊው ጥበቃ እና እንክብካቤ” እየተደረገላቸው እንደሆነ አብራርተዋል።

ታጣቂዎችን ወደ ሥልጠና ማዕከል ለማስገባት እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ምሁራን ያሳዩት ተነሳሽነት የሚደነቅ መኾኑንም አንስተዋል። ለሰላም መስዋዕትነት እንከፍላለን በሚል መሥራታቸውንም ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button