አዲስ አዲስ፣ ነሃሴ 7/2016 ዓ/ም፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የግል ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የደመወዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ መንግሥት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጠየቀ።
የኮንፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰለሞን ዜና፣ “ማሻሻያውን ተከትሎ መንግሥት ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ ካደረገ የግል ድርጅት ሠራተኞችም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ያስፈልጋል” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
“ይህም የኢኮኖሚ ሚዛን እንዲጠበቅ ያግዛል” ያሉት ባለሙያው አክለውም ከዚህ ቀደም በአሰሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 11/56 መሰረት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚወስን ቦርድ እንዲቋቋም መወሰኑን አስታውሰው ነገር ግን እስከአሁን ድረስ ቦርዱ መቋቋም እንዳልቻለ ገልጸዋል።
በኢሠማኮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ሰለሞን ዜና በተጨማሪም የቦርዱ ሃላፊነት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ከመወሰን ባለፈ በየጊዜው ከሚኖሩ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች አንፃር የደመወዝ ወለልን መከለስን ጨምሮ እንደሚያካትት ገልጸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሸያውን ተከትሎ ከሚኖሩ ለውጦች አንፃር ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ይወስናል የተባለው ቦርድ በአስቸኳይ ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባም አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች አስከ 300 ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ገልጸው ለዚህም መንግሥት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቀዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያውን ተከትሎ ይደረጋል የተባለው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንዳይዘገይ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን በቅርቡ አሳስቧል።
የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ተከትሎ በገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑን የገለጸው ኮንፌደሬሽኑ ይህ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ለመንግስት ሰራተኛው ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሽያ ዋጋ የለውም ሲልም አሳስቧል።
“የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል” ሲሉ የገለጹት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዘዳት አያሌው አህመድ፤ መንግስት የደመወዝ ጭማሪ አደርጋለው ቢልም ገበያው በዚሁ ከቀጠለ ከሰራተኛው ከአቅሙ በላይ ሊሆንበት ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። አስ