አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3/ 2026 ዓ/ም፦ በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት ትላንት መጋቢት 2/ 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ስብሰባ፤ የፌደራል መንግስቱ እና ህወሓት ህዳር 2022 በፕሪቶሪያ ለተደረሰው ዘላቂ ግጭት የማስቆም ስምምነት ተግበራ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ትላንት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ከተካሄደው የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ስብሰባ በኋላ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ አካላት “ በትግራይ ክልል ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስቀጠል ሁለገብ ምክክር ለማድረግ እና በየጊዜው ለመመካከር ተስማምተዋል” ብሏል።
በተጨማሪም “በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ተመሳሳይ ስብሰባ ለማድረግ ወስነዋል” ተብሏል።
“የተተገበሩ ሂደቶችን” እውቀና የሰጡት ሁለቱ አካላት፤ “ግጭት የማቆም ስምምነቱን በሙሉ ተግባራዊ ለማደረግ የጋራ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን መለየታቸውን” የህብረቱ መግለጫ አክሎ አስታውቋል።
ቀደም ሲል የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት፤ ስብሰባው ተግዳሮቶችን እና መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚገቡ ቀሪ ጉዳዮችን ለመገምገም አስፈላጊ እና ወቅታዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ፋኪ፣ “ስለዚህ ያልተፈቱ ጉዳዮችን እንዲያወጡና ሊፈቱ የሚችሉበትን አግባብ ለመጠቆም የተሻላችሁ ናችሁ” ብለዋል። እንዲያስቀምጡ” ጠይቀዋል።
ሊቀመንበሩ፤ “እስከ አሁን ድረስ የማይካዱ ስኬቶች ቢኖሩም፤ የፖለቲካ ውይይት ሂደት፣ የሽግግር ፍትሕና የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ መበተንና መልሶ የማዋሃድ ጉዳይ አስቸኳይ ትኩረታችሁን ከሚሹ ጉዳዮች መካከል ናቸው” ብለዋል።
በስብሰባው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት፣ የትግራይ ጊዜያው አስተዳደር/ህወኃት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህበረት፣ የኢጋድ፣ የአሜሪካ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካዮች ያሳተፈ መሆኑ ተገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት የጸጥታና ሰላም ኮሚሽን በመግለጫው፤ የተካሄደው ስብሰባ፤ በዋነኝነት ትኩረቱ የስምምነቱ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ማለትም የሰብዓዊ ረድኤት፣ የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎችን መበተን እና ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ የማድረግ እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ላይ መሆኑን ገልጿል።
ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር በኩል በስምምነቱ አፈጻጻም ዙሪያ በመሰጠት ላይ ያሉ መግለጫዎች በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን የሚያመላክቱ ተደርገው ተወስደዋል።
በህገመንግስቱ እና በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ሙሉ በሙሉ አለመከበሩ፣ በምዕራብ ትግራይ እና በደቡብ ትግራይ አካባቢ የሚገኙ የአማራ ታጣቂዎች እና የኤርትራ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አለመውጣታቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው አለመመለሳቸው የልዩነቶቹ ዋነኛ ነጥቦች ሁነው በመቅረብ ላይ ይገኛሉ። አስ