ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ፍላጎታቸውን “በነፍጥ” ማስፈጸም በሚሹ አካላት ላይ “የተጠናከር ሕግ የማስከበር ሥራ” እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/ 2015 ዓ/ም፦ ብልጽግና ፓርቲ፤ ዓላማቸው “በነፍጥ” ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ “ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ” እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ። ፓርቲው በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ግን ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ ተወስኗል ሲል ገልጿል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ከጥር 13 እስከ 17 ቀን 2016 በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሄድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ማጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል። 

ፓርቲው በመግላጫው የአካባቢያዊ ግጭቶች በመፍታት ሀገራዊ ሰላም ማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል ብሏል፡፡

ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ውሳኔ መተላለፉም ተመላክቷል፡፡

የ2016 የበጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገት 7.9 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዮአል ያለው የፓርቲው መግለጫ ይሄንንም ለማሳካት አመራሩና አባላቱ ከሕዝቡ ጋር በመሆን በቀሪ ጊዜያት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው ተወስኗል በሏል፡፡አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button