ዜናቢዝነስ

ዜና: በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአምስት ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም፡- የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ኦዲት ሪፖርት ላይ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ። በውይይቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተተገበሩ ያሉ የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ መንገዶች መዳሰሳቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ 5 ዓመት በላይ የተከማቸ ዝቃጭ ቆሻሻ መኖሩን ያስታወቀው መረጃው ከፓርኩ ወደ ሀዋሳ ሐይቅ የሚገባ ፍሳሽ አለ መባሉንም ጠቁሟል። ከሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ከቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ እርሻ ማሳ የሚገባ ፍሳሽ መኖሩም በኦዲት ሪፖርቱ መመለካቱን አስታውቋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተጠናላቸው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ውጪ በሆኑ ዘርፎች ሲሰማሩ ተገቢው ጥናት አልተደረገም ተብሏል።

በምርት ሂደት የሚጠቀሙባቸውን ኬሚካሎች ይዘት ለኮርፖሬሽኑና ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚያሳውቁበት መመሪያ አለመኖሩ ተገልጿል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታና የአልሚዎችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለን ማለታቸውን መረጃው አካቷል።

ሀዋሳን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተከማችተው የሚገኙ ዝቃጮችን ወደ ማዳበሪያና ወደ ግንባታ ግብዓት በመቀየር ፓርኮቹን ፅዱ እና አረንጓዴ የማድረግ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ያለው የፓርላማው መረጃ የፍሳሽ ማስወገጃ ታንከሮች በኢንዱስትሪ ፓርክ ደረጃ የተገነቡ ቢሆንም 33 አልሚዎች ጊዜያዊ ማጣሪያዎች እንዲገነቡ መደረጉን ተናግረዋል።

ጊዜያዊ የማጣሪያ ታንከር የሌላቸው የደብረ ብርሃንና ባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርኮች የታንከር ግንባታ በአፋጣኝ ሊጠናቀቅ ይገባል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ማሳሰባቸውን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኮርፖሬሽኑ የተሰጡትን የኦዲት ግኝት ሪፖርቶችና አስተያየቶች ለማረም ያከናወናቸውን ተግባራት እስከ ግንቦት 30 ለምክር ቤቱ እና ለዋና ኦዲተር እንዲያቀርብ መጠየቁን መረጃው ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button