ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የአማራ ክልል መንግስት ከታጣቂዎች ጋር “በየትኛውም አደራዳሪ ወገን ለመደራደር ዝግጁ ነኝ” አለ፣ በክልሉ ሰላማዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመኖሩን አምኗል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር “በየትኛውም አደራዳሪ ወገን ለመደራደር ዝግጁ” መሆኑን አስታወቀ።

የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ደሳለኝ ጣሰው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት “ጫካ የሚገኙ ወንድሞች ለድርድር ጆሮ ሰጥተው የሚመጡ ከኾነ በየትኛውም አደራዳሪ ወገን ለመደራደር ግልጽ የኾነ አቋም” መያዙንም ገልጸዋል።

መንግሥት የሰላም ውይይቱን እና ድርድሩን የፈቀደው “ለፖለቲካ ትርፍ ሳይኾን ለአማራ ሕዝብ ሰላም እና እረፈትን” ለመስጠት ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለሰላም አማራጭ እና ለሰላም ካውንስሉ ያለው አቋም ዛሬም ቢኾን የጸና ነው ያሉት ሃላፊው ለሰላም እና ለድርድር የሚመጡ ሃይሎችን አንድ እርምጃ ሄደው እንደሚቀበሉም አስታውቀዋል።

“የቀረበውን ሃሳብ ለጊዜ መግዣ እና ለዘረፋ እየተጠቀሙበት” ሲሉ በወቀሷቸውና አንዳንድ ሲሉ በጠሯቸው አካላት ላይ “የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ” ይገባልም ብለዋል። ግድያን፣ ዘረፋን እና እገታን ለማስቆም ሕግ የማስከበር ሥራ እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ሰላማዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመኖሩን፣ አርሶ አደሮች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ መደረጋቸውንም ሃላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል።

በአማራ ክልል የተሻሻለ ሰላም አለ ስንል “ሙሉ ለሙሉ ሰላም ተረጋግጧል ማለታችን አይደለም” ያሉት ሃላፊው ደሳለኝ ጣሰው “ሰላማዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፣ አርሶ አደሮች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሠሩ የሚረብሹ ችግሮች አሉ” ሲሉ አስታውቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመግለጫቸው “ክልሉ ከነበረበት የጸጥታ ችግር እየወጣ የተሻለ ሰላም ላይ መኾኑን” ደግሞ ተናግረዋል። የጸጥታ ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንጻር ሲታይ የክልሉ ሰላም ትልቅ መሻሻል ውስጥ መኾኑንም አስታውቀዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ከሕዝቡ ጋር በሠራው ሥራ ክልሉ ተጋርጦበት ከነበረው የመፍረስ አደጋ መውጣቱን ነው ያስታወሱት።

የክልሉን የጸጥታ መዋቅር በማደራጀት እና በመገንባት በራሱ አቅም የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መኾኑንም አስታውቀዋል።

በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር እያጠፋ ያለው በአብሮነት የሚያምነውን እና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን የአማራ ክልልን ሕዝብ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button