ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ግብረ ሀይሉ “በመዲናዋ የሽብር ተግባር ሊፈጽሙ ሲያቅዱ የነበሩ ተጠርጠሪዎችን” በቁጥጥር ሥር አዋልኩ ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር አዋልኩ ሲል የሀገሪቱ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ።

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል በሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በኩል ባሰራጨው መግለጫ እንዳስታወቀው ቡድኑ ቀደም ሲል “አማራ ክልልን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ያዘጋጀው ሴራ ሲከሽፍበት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች” በማምጣት የሁከትና የሽብር ለመፈጸም ሲጥር ነበር ብሏል።

መግለጫው አክሎም፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 50 ተጠርጣሪዎች ውስጥም የቡድኑ መሪ ስንታየሁ ንጋቱ እንደሚባል ጠቁሞ አስተባባሪዎቹም በውጭ ሀራት የሚኖሩት “ሺ አለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፡ ሀብታሙ አያሌው እና መሳይ መኮንን” ናቸው ሲል ገልጿል።

በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሰው “በእስክንድር ነጋ የሚመራው ቡድን” የዚህ ሴራ አካለ ነው ሲል የገለጸው ግብረ ሀይሉ በቁጥጥር ስር ውለው በማረሚያ ቤት የሚገኙ “እነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፡ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው እና ዮርዳኖስ ዓለሜ “ቡድኑን ይመሩት ነበር ብሏል።

መግለጫው አክሎም፤ በቁጥጥር ስር የዋለው የተደራጀው የህቡዕ ቡድን ዋና ማዕከሉን አዲስ አበባ እንዲሁም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ አድርጎ ይንቀሳቀስ ነበር ሲል ጠቁሟል።

ቡድኑ ለአደረጃጀቱ ምቹ ሁኔታ ይፈጥሩልኛል የሚላቸውን አንዳንድ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን” ተከታዮችን በመጠቀም ተቋማትን መሰብሰቢያ እና ማደራጃ በማድረግ በህቡዕ ሲንቀሳቀስ እንደነበር አረጋግጫለሁ ብሏል።

ቡድኑ በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች አባላትን የመመልመልና እና ሎጀስቲክስ የማደራጀት ሥራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ የጠቆመው መግለጫው፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት አምስት ወራት ባካሄደው ጥብቅና ሚስጥራዊ ክትትል እንደተደረሰበት አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ቡድኑና ተባባሪዎቹም፤ በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ በአዲስ አበባና በአዋሳኝ አካባቢዎች ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ ቦንቦች፣ ተቀጣጣይ ቁሶች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች፣ የባንክ ደብተሮች እና የተለያዩ ሰነዶች ጋር መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

ህቡዕ ቡድኑ አደረጃጀቱን ከህዳር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሰነድ በማዘጋጀትና የጋራ መግባባት በመፍጠር የራሱ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ የመረጃ እና ፋይናንስ እንዲሁም የሚዲያ እና የፕሮፖጋንዳ ክንፍ የሚል መዋቅር በመፍጠር ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም ግብረ-ኃይሉ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button