ርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕሰ አንቀጽ፡ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለመጠበቅ እና ወደ ጦርነት የመመለስ አደጋን ለማስወገድ ውጤታማ ክትትል አሁኑኑ ይተግበር!

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/2016 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል የተጀመረውንና በኋላም ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመስፋፋት ለሁለት ዓመት የዘለቀውን አውዳሚ ጦርነት ለማቆም፤ በኢትዮጵያ መንግስትና በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) መካከል፤ የፕሪቶሪያ ጦርነት ማቆም ስምምነት ከተደረሰ አንድ ዓመት ከአራት ወራት ሆኗል።

የስምምነቱ መፈረም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች የተቀበሉት ሲሆን፤ በጋራ እፎይ ያስባለም ነበር። ስምምነቱ፤ በትግራይ ውስጥ የጦር መሳሪያን ድምጽ ዝም ያሰኘ፣ የሰብአዊ እርዳታ ፍሰቱን ያፋጠነ እና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማቋቋም አስችሏል።  

ይሁን እንጂ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለማጽናት የሚጠበቁ  ወሳኝ ግዴታዎች እስካሁን ባለመፈፀማቸው፤ በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ባለሥልጣናት መካከል ያለው ልዩነት እንዲሰፋ አድርጓል። የትግበራ ሂደቱ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ተፈጻሚ ካልተደረገ፤ ወደ ግጭት የመመለሱ ነገር፤ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ይሆናል።

የፌዴራል መንግስት፤ የኤርትራ ኃይሎች ከሰሜን ምስራቅ ትግራይ ክልል አካባቢዎች መውጣትን በተመለከተ እንደ የተከለከለ ጉዳይ በመቁጠር፤ በጦርነቱ ወቅት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከቀረቡ ቁልፍ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዳይወጣ አድርጓል ነው።

መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ የሆነው አመታዊው የአሜሪካ የደህንነት ማህበረሰብ የስጋት ምዘና ሪፖርት፤ “የፕሪቶርያው ስምምነት፤ በኢትዮጵያ የተካሄደውን አውዳሚ ጦርነት ማስቆም ቢችልም፤ በአማራ ክልል ኃይሎች ስር የሚገኙ ምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ አካባቢ ያለው የወሰን ጉዳዮች እልባት አለማግኘታቸው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል” ሲል አስጠንቅቋል።  ይህም ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቃዮችን እና ሱዳን ውስጥ ለድርብ መከራ የተጋለጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ስደተኞችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንቅፋት ሆኗል።

የፌዴራል መንግስት፤ የኤርትራ ኃይሎች ከሰሜን ምስራቅ ትግራይ ክልል አካባቢዎች መውጣትን በተመለከተ እንደ የተከለከለ ጉዳይ በመቁጠር፤ በጦርነቱ ወቅት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከቀረቡ ቁልፍ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዳይወጣ አድርጓል ነው።  የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ተልዕኮ ማስከበር ኬሚቴ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ  የትግራይ ኃይሎችን ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆን ትጥቅ የማስፈታት ስራ መፈፀሙን አስታወቋል። የፌደራል መንግስት የውጭ ኃይሎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያልሆኑ ኃይሎች ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ የመቆጣጠር ስራው ከዚህ ጋር እኩል እየሄደ አይደለም። 

የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን፤ ቀላል መሳሪያዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ማቋቋም (DDR) ሂደት መጓተት፤ የስምምነቱ ፈጻሚዎች መካከል የጦርነቱ መንስዔ ላይ ትርጉም ያለው የፖለቲካ ውይይት ካለማድረጋቸው ጋር ተደምሮ ሁለቱ አካላት መካከለ አለመተማመን እና ጥርጣሬን አስከትሏል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በእነዚህም ውስብስብ ጉዳዮች፤ ሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች፣ የጦር ወንጀሎች እና በኃይል የማፈናቀል ወንጀሎች ተብሎው ለተፈረጁ ወንጀሎች ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ፍትህ እና ተጠያቂነት የማስፈጸም ጉዳይ ችላ ተብሏል። 

በተንቀራፈፈ ሁኔታ ተፈጻሚ እየሆነ ላለው የሰላም ስምምነት በዋናነት ተፈራራሚ አካላት ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ቢሆንም ለስምምነቱ መደረስ የአንበሳውን ድርሻ የተሰጠው የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎቹ ባለድርሻ አካላት በተለይም አሜሪካ እና ቀጠናዊው ተቋም ኢጋድ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይችሉም፤ ዲፕሎማሲያዊ መንገድን በተከተለ መልኩ ውጤታማ የሆነ የክትትል እንዲኖር ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር። በተለይም በከፍተኛ ሞያተኞች አማካኝነት የክትትል፣ የማረጋገጥና ተልዕኮ የማስከበር ስራን እንዲያከናውን ሃላፊነት የተሰጠው የአፍሪካ ህብረት ሃላፊነቱን ትቶት ከርሟል።

ይህ ውድቀት መውጣት የጀመርው በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ልዩነቶች እየሰፉ መውጣት መጀመራቸውን ተከትሎ ነበር፣ በተጨማሪም በተከታታይ የሚዲያ ዘመቻዎች መካሄዳቸውን ተከትሎ ነው። ይህም በስምምነቱን ለማስተግበር በተፈራራሚዎቹ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን መተማመን ከመሸርሸር ባለፈ ወደ መጠላለቱ ለመግባት ያለውን እድል እዳያሰፋ ያሰጋል።

ትኩረቱን የስምምነቱ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ማለትም የሰብዓዊ ረድኤት፣ የትጥቅ መፍታት፣ ታጣቂዎችን መበተን እና ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ የማድረግ እንዲሁም የመልሶ ግንባታ ላይ ያደረገው የመጀመሪያው የስትራቴጂ ግምገማው የተካሄደው ስምምነቱ ከተፈጸመ ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ነው። 

ህብረቱ የመጀመሪያ ስትራቴጂያዊ ግምገማ ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ ተደራዳሪዎቹ ስምምነቱን ለማስፈጸም አሁንም ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፣ በየግዜው እየተገናኙ ለመነጋገርም ተስማምተዋል ከሚለው ቁምነገር የዘለለ ባልተፈጸሙ የስምምነቱ ነጥቦችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ዝርዝር አፈጻጸም ወይንም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አካሄድ መቀመጡን የሚያሳይ ምን አይነት መረጃ አላቀረበም።

የጋራ ኮሚቴው እና የባለሞያተኞቹም ቡድን ቢሆን በሰላም ስምምነቱ መሰረት የክትትል፣ የማረጋገጥና ተልዕኮ የማስከበር ስራን እንዲያከናውን ሃላፊነ የተሰጣቸው ቢሆንም ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረጉ አልነበረም፤ የትግራይ ተዋጊዎች ለፌደራል መንግስት ሰራዊቱ ከባድ መሳሪያዎችን ባስረከቡበት ሁለት ጊዜያት ብቻ ለእይታ ቀርበዋል።  ይህ ችግር መውጣት የጀመርው በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ልዩነቶች እየሰፉ መውጣት መጀመራቸውን ተከትሎ ነበር፣ በተጨማሪም በተከታታይ የሚዲያ ዘመቻዎች መካሄዳቸውን ተከትሎ ነው። ይህም በስምምነቱን ለማስተግበር በተፈራራሚዎቹ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን መተማመን ከመሸርሸር ባለፈ ወደ መጠላለቱ ለመግባት ያለውን እድል እዳያሰፋ ያሰጋል።

ለምሳሌ፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በአውሮፓ ከኤርትራና ከግብፅ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል በሚል የሚነሱ ውንጀላዎች ከባድና ብዙ መዘዝ ያስከትላሉ። 

የፕሪቶሪያ ስምምነት ወደ መዳከም እያደገ መሆኑን የሚያመለክቱ በቂ ማሳያዎች አሉ፤  አተገባበሩ ላይ ውጤታማ ክትትል እና የተጠያቂነት አሰራር ከሌለው ይፈርሳል።  

ስምምነቱ አንቀጽ 3(3) እንደሚያመላክተው ስምምነቱ ሁሉንም አይነት የፕሮፓጋንዳ እና የጥላቻ ንግግሮች ማቆምን ያጠቃለለ ሲሆን፤ በአንቀጽ 11(8) መሰረት ደግሞ፤ ጥሰት በሚፈፀምበት ጊዜ የባለሙያዎች ቡድን ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ጥሰቱን ለማስተካከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ያሳውቃል። በተጨማሪም፤ በአንቀጽ 11(9) ስርም ጥሰቱ በ24 ሰዓታት ውስጥ ካልተስተካከለ የአፍሪካ ህብረት በከፍተኛ ጉባኤው አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት የጋራ ኮሚቴው እንደሚሰበስብ ተገልጿል። ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚታይ ተግባር አልተወሰደም። ከዚህ ይልቅ ከፍተኛ የሆነ የመገናኛ ብዙኃን ዘመቻ በመካሄ ላይ መሆኑ፤ የተገኘውን ውስን ውጤት አደጋ ላይ ይጥላል።

ሁለቱ አካላት ካልተረጋገጡ ውንጀላዎች መታቀብ እና ካላስፈላጊ ንግግሮች መቆጠብ የግድ አስፈላጊ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም የሰላም ስምምነቱ እንዳይፈርስ እና ወደ አዲስ ግጭት እንዳይገባ ለመከላከል እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጥሰቶችን ለመለየት፤ የክትትል፣ የማርጋገጥ እና ተልዕኮ ማስከበር አሠራር ውጤታማ በሆነ መንገድ መሥራቱ አስፈላጊ ነው።

በቅርቡ የተደረገው ስትራቴጂካዊ ግምገማ በትክክለኛው አቅጣጫ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል። ነገር ግን የአፍሪካ ኅብረት እና ሌሎች የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት የስምምነቱን ሙሉ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የየራሳቸውን ቁርጠኝነት ካልጠበቁ በስተቀር ዘላቂ ሰላም የማስፈኑ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል።

የፕሪቶሪያ ስምምነት ወደ መዳከም እያደገ መሆኑን የሚያመለክቱ በቂ ምልክቶች አሉ፤ አተገባበሩ ላይ ውጤታማ ክትትል እና የተጠያቂነት አሰራር ከሌለው ይፈርሳል። ስምምነቱ በራሱ ፍጹም ባይሆንም፣ የመፍረሱ ውጤት ግን አስከፊ ይሆናሉ።አስ

ተጨማሪ አሳይ
Back to top button