ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም፡-የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ መገደላቸው ተገለጸ። ከወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዋና አስተዳዳሪው የተገደሉ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ነው።

“ፅንፈኛ አካላት በምሽት ተሹለክልከው በመግባት የወረዳችንን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ህይወት ቀጥፈውታል” ሲል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮው ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።

የተገደሉት አስተዳዳሪው አቶ አልብስ በአከባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ የወደሙ የጤናና ሌሎች ተቋማትንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመስራት መልሶ ለማቋቋም ጥረት እያደረገ የነበረ መሪ ነው ሲል ወረዳው በሀዘን መግለጫው ጠቁሟል።

የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳደር የህግ የበላይነትንና ሰላምን የማረጋገጥ፣ የተጀመሩና የተጎዱ የልማት ስራዎችን የማነቃቃትና የማሻሻል ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚሰራ አስታውቆ በፅንፈኞች ሴራና በመሪ ግድያ የሚቆም ነገር የለም ብሏል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ እናና የወረዳው የፀጥታ አካላት የፅንፈኛ ሀይሉን የማፅዳትና ለሕብረተሰባችን እረፍት የመስጠት እርምጃውን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲል ወረዳው በኮሙዩኒኬሽን ቢሮው በኩል ባሰራጨው መረጃ ጠይቋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ግድያዎች መፈፀማቸው የሚታወቀ ሲሆን ባሳለፍነው ሰኔ ወር በሸዋሮቢት ከተማ ሁለት የተለያዩ የመንግስት የፀጥታ ዘርፍ የስራ ሃላፊዎች መገደላቸው አይዘነጋም፡፡

ማክሰኞ ሰኔ 27 የከተማ አስተዳደሩ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ተገድለዋል፡፡ በተጨማሪም ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ሰኔ 29 ቀን ማታ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት በስራ ላይ እያሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተደግለዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሓምሌ 8 ቀን አብዱልከሪም አባጀበል የተባለ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቀ ሀይሎች በጥይት መገደሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከዚህ ቀደም የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው በተለያያ ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው አይዘነጋም፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button