ዜናቢዝነስ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5/2016 ዓ.ም፡-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀረበውን የ2017 የፌዴራል መንግስት የካፒታል እና የመደበኛ ረቂቅ በጀት መግለጫ አድምጧል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 ረቂቅ በጀት መግለጫ (Budget speech) በዝርዝር ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚህም የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት በጀት 9 መቶ 71 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸው፤ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ21 ነጥብ1 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም ለመደበኛ በጀት የዓመቱ የወጪ በጀት 451.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን ለካፒታል ደግሞ 283.2 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

ለክልል መንግስታት ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚሆን የበጀት ድጋፍ ለማድረግ በረቂቅ አዋጁ ላይ መመላከቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ከፕሮጀክቶች ፍትሃዊ አቅርቦትና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ፤ ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ዓመታት የመንገድ እና ውሃ ፕሮጀክቶች ስርጭት በሁሉም አካባቢዎች ፍትሃዊ የሆነ የልማት ተደራሽ እንዲኖር ለማደረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

መንግስት የዕዳ ጫናውን ለመቀነስ ትኩረት በመስጠት ለመደበኛው በጀት ከፍተኛ ገንዘብ መመደብ መቻሉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የዋጋ ንረቱ የኢኮኖሚውን ዕድገት ስለሚጎዳው በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ አሉታዊ ጫናው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሉም አካላት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከዋጋ ንረትና ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር በተያያዘ እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ምርትና ምርታማነትን ለመሳደግ የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል በበጀት መደግፍ እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አመላክተዋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ጫናን ለመቀነስ የጥቁር ገበያውን የዋጋ ጭማሬ በመቆጣጠር እና የሀገርን የውስጥ የገቢ አቅም ለማሳደግ ሚኒስቴር መስሪ ቤት የገቢ አሳባሰብ ስርአትን ለማሻሻል ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ መሆን እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት አመላክተዋል፡፡

በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የትምህርት፣ የጤናና የመብራት ተደራሽነትን መልሶ ለመጠገን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን በጀት መመደብ እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡

ለ2017 በጀት አመት የቀረበውን ረቂቅ በጀት፤ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button