ህግ እና ፍትህማህበራዊ ጉዳይርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕስ አንቀፅ: እየተባባሰ የመጣው በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰው ፆታዊ ጥቃት የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ትስስር እየተሸረሸረ ለመምጣቱ ማሳያ ነው፣ ተጠያቂነት ማስፈን ካልተቻለ አደገኛ መዘዝ ይዞ ይመጣል!

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም፡- ባለፈው አመት ነሃሴ ወር ላይ በህጻን ሔቨን አወት ላይ የተፈጸመው ታሪክ ባሳለፍነው ሳምንት መሰማቱን ተከትሎ መላ ሀገሪቱን ያስደነገጠ ክስተት ሆኖ ሰንብቷል።  የሰባት አመት ህጻኗ፤ የእናቷ መኖሪያ ቤት አከራይና የሶስት ልጆች አባት በሆነው ጌትነት ባይህ አስገድዶ መድፈር እና ግድያ ወንጀል እንደተፈጸመባት ነው የተገለጸው።

አስከሬኗ በገኘበት ወቅት አንገቷ መታነቁን፣ የሰውነት ክፍሎቿ መቆራረጣቸውን እና አፏ በአሸዋና ጨርቅ ተጠቅጥቆ ነበር። የሄቨን ደፋሪ እና ነፍሰ ገዳይ በአማራ ክልል ፍርድ ቤት የ25 አመት እስራት ብቻ እንዲቀጣ የተበየነበት ሲሆን ይግባኝ ጠይቋል። በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመው ተግባር በህብረተሰቡ ዘንድ ታላቅ ቁጣ ከመቀስቀሱ ባሻገር ወንጀል ፈጻሚው የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚጠይቁ ዘመቻዎች ተካሂደዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ልዩ ታሪክና የበለጸገ የባህል ቅርስ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ትገኛለች። በተለይም ሀገሪቱ በብዙ ነገሮች እንድትታወቅ ባደረጉት በሶስቱ ትላልቅ ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የተከሰቱ ችግሮች ሁሉንም እንዳልነበር የሚያደርጉ ናቸው።

በእነዚህ ግጭቶች ሳቢያ የሚከሰቱ አብዘሃኛዎቹ አጥፊ ውድመቶች ጥላሸታቸው ከጦር ሜዳዎች አልፎ የሚሄድ ነው። ለአብነት ያክል በሀገሪቱ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸመው የፆታ ጥቃት መጥቀስ ይቻላል።  ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸመው የፆታ ጥቃት ወደ ህብረተሰቡ መዋቅር ውስጥ እየገባ እና ለመግለጽ የሚያስቸግር ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በጣም የሚያስደነግጠው ጉዳይ የዚህ አሰቃቂ ጥቃት ዋነኛ ምክንያት ጦርነት የሚያስከትለው መዘዝ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ እንደ ጦርነት ስትራቴጂ በመጠቀም መንግስት አጥፊዎችን ተጠያቂ ባለማድረጉ ጥቃቱ እንዲበረታ ምክንያት በመሆኑ ነው።

ይህ ሁኔታ ከትግራይ ክልል የበለጠ የትም አልታየም፤ የተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች ሴቶች እና ልጃገረዶች ስልታዊ በሆነ መንገድ ፆታዊ ጥቃትን እንደ የጦርነት መሳሪያነት ሲጠቀሙበት ታይቷል።

ተልዕኮው የተጠናቀቀው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን (ICHREE) በያዝነው አመት በመስከረም እና ጥቅምት ወር ላይ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት 54ኛ ስብሰባ ባቀረበው ሪፖርት በትግራይ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ወቅት በክልሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ አሰቃቂ የሆነ ጾታዊ ጥቃት በመፈጸም እንደጦር ስልት ጥቅም ላይ መዋሉን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“በትግራይ በተለያዩ ግዜያት በተካሄዱ ጦርነቶች በሁሉም የክልሉ ዞኖች በሴቶች እና ህጻናት ላይ በሰፊው እና ሆን ተብሎ እንደ ስልት የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን መመዝገቡን አመላክቷል።  እነዚህ ተግባራት በዋናነት የተፈጸሙት

በኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ አብዘሃኛውን ግዜ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር፣ በአማራ ልዩ ሀይል፣ በአፋር ልዩ ሀይል እና በፋኖ ታጣቂዎች ነበር።አብዘሃኛዎች አስገድዶ መድፈሮች የተፈጸሙት የተለያዩ የታጣቁ ቡድኖች አባላት በተሳተፉበት ሲሆን ይህም የታጣቂ ቡድኖቹ በመተባበር እንደፈጸሙት የሚያሳይ ነው” ሲል ሪፖርቱ አመላክቷል።

ምንም እንኳን በተመሳሳይ መጠን እና አላማ ባይሆንም፣ በሚያሳዝን ሁኔታ የክልሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከፕሪቶርያው ስምምነት በኋላም ቢሆን ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ስቃይ ደርሶባቸዋል።

እንደ ህብረተሰብ አሁን ላይ የደረስንበት ደረጃ፣ ድርጊት ፈጻሚዎች ቅጣት ስላልተላለፈባቸው የፆታዊ ጥቃትን አዙሪት ከማስቀጠል ባለፈ የሚፈይደው ነገር የለም። መሰል ወንጀሎች በጦርነት ወቅቶች ሲፈጸሙ እንዲሁ ያለተጠያቂነት እንዲታለፉ እንደሚደረግ የሚጠቁሙ መልዕክቶች በሚያስተላልፍ መንገድ እንዲስተናገዱ መደረጉ፣ ከጦርነት አውድ ውጭ ሊስፋፋ የሚያስችል አደገኛ መልእክት የሚያስተላልፍበት አካኋነ በመፍጠር ላይ እንገኛለን።

አለምአቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት “የትግራይ ሀይሎች በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ የአማራ ክልል አከባቢዎች በተለይም ጪና በተባለች መንደር አስገድዶ መድፈር እና የተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች በሰፊው መፈጸማቸውን አስታውቋል። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት የተካተቱት 30 የሚሆኑ ተያያዥ የሆኑ ምርመራዎች በርካታ የሚሆኑ የትግራይ ታጣቂዎች በተለያዩ ቦታዎች የፈጸሙት ተመሳሳይ ጥቃቶች አካል ነው” ብሏል።

ምናልባትም ከሁሉም በላይ አሳሳቢ የሚሆነው ጉዳይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህን አስከፊ ወንጀሎች ለመፍታት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጉ ነው። በአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃን በርካታ ሰነዶችን ይፋ ቢያደርጉም መንግስት ወንጀሉን ፈጻሚዎች ላይ ምርመራ ለማካሄድ፣ ክስ ለመመስረትም ሆነ ቅጣት ለማስተላለፍ ያደረገው ጥረት እጅግ አናሳ ነው።

እንደ ህብረተሰብ አሁን ላይ የደረስንበት ደረጃ፣ ድርጊት ፈጻሚዎች ቅጣት ስላልተላለፈባቸው የፆታዊ ጥቃትን አዙሪት ከማስቀጠል ባለፈ የሚፈይደው ነገር የለም። መሰል ወንጀሎች በጦርነት ወቅቶች ሲፈጸሙ እንዲሁ ያለተጠያቂነት እንዲታለፉ እንደሚደረግ የሚጠቁሙ መልዕክቶች በሚያስተላልፍ መንገድ ትሪት መደረጉ፣ ከጦርነት አውድ ውጭ ሊስፋፋ የሚያስችል አደገኛ መልእክት የሚያስተላልፍበት አካኋነ በመፍጠር ላይ እንገኛለን።

እርምጃ አለመወሰዱ የሞራል ውድቀት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅን ህሊና የሚያቆሽሽ ተግባር ነው፤ በተጨማሪም  በአለም አቀፍ ህግጋት መሰረት ኢትዮጵያ ልታስከብረው የሚገባትን አለመፈጸሟን የሚያሳብቅ እና በሀገሪቱ ጾታን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ ተሟጋች ቡድኖች የጋራ ውድቀት ነው።

የሄቨን ታሪክ የእያንዳዱን ኢትዮጵያዊ ቤት እያንኳኳ እና የኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ትስስርን እየሸረሸረው የሚገኘው ጥቃት አድራሾች ላይ ቅጣት ባለመተላለፉ የሚፈጸም ወንጀል ታሪክ አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ወንጀለኞችን በህግ ፊት ተጠያቂ ማድረግ አለመቻሉ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን የመጠበቅ ሃላፊነትን አለመወጣቱን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን ፍትህን የማስከበር እና ወንጀለኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ዳተኛ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

በታዳጊዋ ሄቨን አወት ላይ ከተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር የተሻለ ይህንን ውድቀት ምንም አይነት ጉዳይ ሊገልጸው አይችልም።

የሄቨን አሳዛኝ ታሪክ ለአደባባይ የበቃው በኢትዮጵያ ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል በሚል በሚንቀሳቀሱ የመብት ተሟጋች ተቋማት አልያም መንግስት በቢሊየን የሚቆጠር በጀት በሚመደብላቸው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሳይሆን እናቷ አበቅየለሽ አዴባ ሚዲያው አቤት እንዲልላት ደፍራ በመውጣቷ ነው።

የሄቨን ታሪክ የእያንዳዱን ኢትዮጵያዊ ቤት እያንኳኳ የሚገኘው እና የኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ትስስር እየተሸረሸረው የሚገኘው ጥቃት አድራሾች ላይ ቅጣት ባለመተላለፉ የሚፈጸም ወንጀል ታሪክ አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ችግር ለመፍታት ቆራጥ እርምጃ መውሰድ አለበት።

በመጀመሪያ ደረጃ በግጭት ቀጠና ውስጥ በሚገኙ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ፆታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ወንጀለኞች በአፋጣኝ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ለፍርድ የማቅረብ አሰራር ሊዘረጋ ይገባል። ይህም ግጭት በሌለባቸው አከባቢዎች የተለመደ እና አዲስ ያልሆ ተግባር ተደርጎ የመቁጠር አዝማሚያን ለመከላከል ይጠቅማል።

ይህም ሁሉንም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች አካታች እና ግልጽነት ባለው መልኩ ተጠያቂ የሚያደርግ፣ ማንም ይሁን ምንም (የስልጣን ደረጃውም ሆነ ወገንተኝነቱ) አጥፊ እስከሆነ ድረስ ወደ ፍርድ ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆንን ያካተተ መሆን ይገባዋል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብም ሊጫወተው የሚገባ ሚና አለው። የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህን ወንጀሎች አጣርቶ ለህግ የማቅረብ ግዴታውን እንዲወጣ እና እየተስተዋለ ያለውን ወንጀለኞችን ተጠያቂ ያለማድረገ አባዜ እንዲቋረጥ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል።

ሴቶች የሰው ልጅ ግማሽ አካል ብቻ ሳይኑ ቀሪውን ግማሹንም የወለዱ ናቸው የሚለውን የቀድሞው የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ጠንከር ያለ አገላለጽ መጠቀም ያስፈልጋል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብም ሊጫወተው የሚገባ ሚና አለው። የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህን ወንጀሎች አጣርቶ ለህግ የማቅረብ ግዴታውን እንዲወጣ እና እየተስተዋለ ያለውን ወንጀለኞችን ተጠያቂ ያለማድረገ አባዜ እንዲቋረጥ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል።

በጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት አካላዊ ብቻ ሳይሆን ስነ ልቦናዊ፣ ቤተሰብን እና ማህበረሰብን እየከፋፈለ ለመሆኑን በግልጽ መናገር ያስፈልጋል።

ጉዳቱን መቀልበስ ቢያዳግትም፣ ቢቻል እንኳ ጠባሳዎቹን ለማከም የብዙ ትውልድን ዘመን ሊጠይቅ ቢችልም፤ ጊዜው ሳይረፍድ ተጎጂዎች ህይወታቸውን ዳግም እንዲመሰርቱ እንዲሁም የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ትስስር እንዳይሸረሸር ማድረግ ይቻላል።

ሊወሰዱ ከሚችሉ እርምጃዎች መካከል የህክምና እንክብካቤን ጨምሮ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ በማድረግ ከእንደዚህ አይነት ወንጀሎች የተረፉት መርዳት ይቻላል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button