ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ሶማሊያ ኢትዮጵያ “ግዛቶቼን ይዛለች” ስትል ከሰሰች፤ "ህጋዊና ከህጋዊ ውጪ” መንገዶችን እንደምትጠቀም ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 27/ 2016 ዓ/ም፦ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ባለስልጣናት ከጸባጫሪ ንግግሮች እንዲቆጠቡ እያሳሳበች ባለችበት ወቅስ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ኢትዮጵያ “የሶማሊያን ግዛቶች መያዟን እንደቀጠለች” በመግለጽ ይህ አካሄድ በሚቀጥሉት ወራት “ህጋዊ እና ከህጋዊ ውጪ” የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ይቆማል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

“ኢትዮጵያ የሶማሊያን ግዛቶች እንደያዘች” የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ “ይህም መፍትሄ ያልተገኘለት ጉዳይ ሆኖ ሳለ አሁን ደግሞ የበለጠ ግዛቶችን ለመያዝ ህልም አላት” ሲሉ ከሰዋል።

አክለውም ሶማሊያ ኢትዮጵያን በኃይል ወደ ባህር እንድትደርስ እንደማትፈቅድ መናገራቸውን የፑትላንዱ ጋሮዌ  ኦንላይን ሚዲያ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለጹት፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም. በወቅታዊ አከባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ፤ “አንዳንድ የሶማሊያ ተወካዮች ልዩነት ማስፋት የአዘቦት ተግባራቸው አድርገውታል።” ሲሉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።

የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በወቅቱ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፤ “የኢትዮጵያ ሰራዊት ሶማሊያ እንደ ሃገር እንድትቆም በርካታ መስዋዕትነት ቢከፍልም፤ አንዳንድ የሶማሊያ መንግሥት ተወካዮች የሰራዊቱን ስም ማጠልሸት የንግግራቸው ማዕከል አድርገውታል።” ሲሉ ከሰዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ያላት መልካም ግኑኝነት ወደ ውጥረት ተቀይሯል። ካይሮ እና ሞቃዲሹ የደረሱትን ወታደራዊ ስምምነት ተከትሎ ግብጽ በሶማሊያ የጦር መሳሪያዎችንና ወታደሮችን በማሰማራቷ ምክንያት በቀጠናው የተፈጠረው ውጥረት እንዲያይል አድርጓል።

በሶማሊያ የግብጽ ጦር መስፈሩን የተቃወሙ የፕሬዝዳንቱ ልዩ ልዑክ እና የምክር ቤት አባል አብዲረሺድ ሞሃመድ ኑር ጂሌይ ከሃላፊነት መነሳታቸውን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የግብጽ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ መግባቱን የሚቃወም መግለጫ የሰጡት የሳውዝ ዌስት ግዛት የፓርላማ ቤት አባል አብዲረሺድ ሞሃመድ ኑር ጂሌይ፤ ሲያገለግሉ ከነበረበት “የጤና እና ስነ ምግብ ልዩ ልዑክ” ኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯል።

ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር ከምትዋሰነው የሳውዝ ዌስት ግዛት የተወከሉ የፌደራል ፓርላማ አባላት ግብጽ እና ሶማሊያ የተፈራረሙትን ወታደራዊ ስምምነት፤ “የናይል ጉዳይ”ን ወደ ሶማሊያ የሚያመጣ እና “በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጦርነትን ሊያመጣ የሚችል” ሲሉ ተቃውመዋል።

በተጨማሪም ቪላ ሶማሊያ የሳውዝ ዌስት ክልልን በፌዴራል ፓርላማ ከሚወክሉ 25 የፓርላማ አባላት ላይ ያለመከሰስ መብታቸውን እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን የፑንት ላንድ ሚዲያ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በመግለጫው፤ በሶማሊያ ህዝብ ደህንነት እና ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠውን ስጋት ለመከላከል መላው ዜጋ እንዲሁም ባለስልጣናት ዝግጁ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ አርብ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም በወቅታዊ አከባቢያዊ ጉዳዮች በሰጡት ማብራሪያ ላይ “ሶማሊያ የቀጠናውን ሰላም ከማይፈልጉ አካላት ጋር የምታደርገው እንቅስቃሴ ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይደለም” ሲሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button