ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በሀገሪቱ በ2023 ከተመዘገቡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተፈጸሙ ናቸው - የመንግስታቱ ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም፡-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታን አስመልክቶ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች የሚፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሳሳቢ ናቸው ብሏል።

በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ የነበረው የሰብአዊ መብት ሁኔታ የተሻሻለ ቢሆንም ኢትዮጵያ በ2023 ፈተና የተሞላበት ሁኔታ አልፋለች ሲል ገልጿል። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ አብዘሃኛዎቹ የኦሮምያ እና የአማራ ክልል አከባቢዎች በከፍተኛ ግጭቶች እና ውጊያዎች የተሞሎ መሆናቸው ነው ብሏል።

በዘፈቀደ የዜጎችን መብት መግፈፍ፣ በፖለቲካ ምክንያት የሚደርስ የአካል ማጉደል፣ የወሲብ ጥቃት፣ የመሰብሰብ ነጻነትን መግፈፍ፣ የዘፈቀደ እስር፣ የመናገር ነጻነት መግፈፍ እገታ እና መሰወር የመሳሰሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ በ2023 መመዝገባቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ በተደጋጋሚ ከተጣሱ ሰብአዊ መብቶች መካከል ዋናዋናዎቹ የዘፈቀደ እስር እና የንጹሃን ግድያዎች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ ይፋ ባደረገው 24 ገጽ ሪፖርቱ እንዳመላከተው በ2023 በኢትዮጵያ 594 የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተፈጸሙ ሁነቶች መመዝገቡን ጠቁሟል፤ በእነዚህ በተመዘገቡት የጥቃት ሁነቶችም 8ሺ 253 ኢትዮጵያውያንን ተጠቂ መሆናቸውን ገልጿል። ከቀደመው አመት ጋር ሲነጻጸር የ56 በመቶ የሚጠጋ የሰብአዊ መብት ጥሰት ጭማሪ ታይቶበታል ብሏል።

የጥቃቱን 70 በመቶ ፈጻሚዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ማለትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የፌደራል እና ክልል ፖሊስ አባላት እና በመንግስት የሚደገፉ የሚሊሻ ታጣቂዎች ናቸው ሲል አስታውቋል፤ 7ሺ 103 ተጠቂዎች የነዚህ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ሰለባዎች ናቸው ሲል ጠቁሟል።

በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ነው ያለው ሪፖርቱ በ2023 ብቻ 740 ንጹሃን ሰዎች በክልሉ መንግስት ከፋኖ ሀይሎች ጋር እያደረገው ባለው ውጊያ መሞታቸው ተመዝግቧል ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በ2023 በኦሮምያ ክልል የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር እያካሂዱት ባለው ውጊያ የ366 ንጹሃን ሞት መመዝገቡን እና ከነዚህም ውስጥ 46 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን አመላክቷል።

በኦሮምያ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል ከሚካሄደው ግጭት በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሞ የሚሊሻ ታጣቂዎች መካከልም ውጊያዎች መካሄዳቸውን ጠቁሟል፤ በኦሮያ እና በሶማሊያ ታጣቂ ሀይሎችም እንዲሁ። ይህም ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል ሲል አስታውቋል።

የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት በተጨማሪ የፌደራል መንግስቱ የመከላከያ ሀይል የድሮን ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ እንዳሳሰበው አመላክቷል።

በ2023 በአምስት ወራት ብቻ በመከላከያ ሀይል በድሮን የተፈጸሙ 18 ጥቃቶች መመዝገቡን አስታውቆ በእነዚህም ጥቃቶች 248 ሰዎች መገደላቸውን 55 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁሟል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል ያለው የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት በዋናነት የዘፈቀደ እስሩ የተፈጸመባቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው ብሏል።

በሀገሪቱ በሚገኙ 16 የማጎሪያ ማዕከላት 5ሺ የሚጠጉትን መመዝገቡን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button