ህግ እና ፍትህዜና

ዜና፡ በሶማሌ ክልል መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 6 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9/ 2017 ዓ/ም፦ በሶማሌ ክልል ዋርዴር ከተማ ትናንት መስከረም 8/2016 ዓ.ም መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 6 ግለሰቦች መገደላቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የከተማው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ረቡዕ ንጋት 10 ሰዓት ገደማ በዋርዴር  ከተማ 04 ቀበሌ በሚገኘው መስጊድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጩ እንደገለጹት፤ “ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ” ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ስድስት ተማሪዎች በመስጂዱ ውስጥ እንደነበሩ ተናግረዋል።

ነዋሪው አክለውም በአካባቢው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በላይ በመሬት ባለቤትነት ውዝግብ ምክንያት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ ግጭቶች መከሰታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪ ከጥቃቱ ከመፈጸሙ አንድ ቀን በፊት የመንግስት ባለስልጣናት እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሰብስበው ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ምንጩ ገልጸዋል።

ይህ ስምምነት የካሳ ክፍያን እንዲሁም ለቀብር የሚወጡ ወጪዎችን ያካተተ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን ለማቆም መስማማታቸውን ገልጸዋል።

“ይሁን እንጂ በማግስቱ  በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ህይወት አልፏል” ብለዋል ነዋሪው።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ምንጩ አክለውም ጥቃት አድራሹ በቁጥጥር ስር ባይውልም ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ መመለሷን እና የጸጥታ ሃይሎች ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።

የሶማሌ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላቅፊ ደይብ አህመድ ጥቃት መፈጸሙን እና ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ድርጊቱ የተፈጠረው በጎሳ ግጭት ነው መባሉ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።

“መንግስት ጉዳዩን አርግቧል” ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

ደይብ ጥቃቱ የተፈጸመው “ሁኔታውን መጠቀም የፈለጉ” እና “የራሳቸው አጀንዳ ባላቸው” ግለሰቦች ሊሆን እንደሚችል  ገልጸዋል።

አክለውም መንግስት ጥቃት አድራሾቹ “ከአልሸባብ ጋር ግንኝነት ያላቸው ሊሆኑ ወይም የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው እና መንግስትን መውቀስ የሚግፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ ገልጸው፤ መንግስት ምርመራ እንደሚያደግ ገልጸዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button