ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአላማጣ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፤ ነዋሪዎቹ የህወሓት ታጣቂዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4/ 2016 ዓ/ም፦ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች የመብራት ኃይል ሰራተኛ  “በህወሃት ታጣቂዎች” ተገድሏል በማሉን ተከትሎ ባደረጉት ሰልፍ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ። 

ሰልፉ በተካሄደበት ቀን አንድ ሰው ላይ ጉዳት ሲደርስ በቀጣዩ ቀን ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፤ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኛ መሞቱን ተከትሎ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 20216 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ በአላማጣ ከተማ ተካሄዷል።

“በተቃውሞው ሰልፉ ወቅት አንድ ሰው ሲገደል፤ ሌላ አንድ ነዋሪ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ቆስለዋል” ሲል ነዋሪው ገልጿል።

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ፤  ሰልፉ የተጠራው የህወሓት ኃይሎች ከአላማጣ እና ከአካባቢው እንዲወጡ ለመጠየቅ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ  ገልጿል።  ነዋሪው “እየተፈጸሙ ያሉ አፈና፣ ግድያ እና ጥቃቶች ያስከተሉት ፍርሃትና ስጋት ለጥያቄው ምክንያት መሆኑን” አክሎ ተናግሯል።

የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊ ሀይሉ አበራ ነዋሪዎቹ እየገጠማቸው የለውን ጥቃቶች በመግለጽ የነዋሪዎቹን ስጋት ገልጸዋል።

ባለፉት ወራት በአላማጣ እና በአቅራቢያው በምትገኘው ኮረም ከተማ ውስጥ የእገታና ግድያ ወንጀል ድርጊቶች መበራከታቸውን፣ ነዋሪዎቹ “ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑንና ከእገታ ለመለቀቀ ክፍያ እንዲከፍሉ” እየተገደዱ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“የደደረገው ሰልፍ ሌላ ሞት እና ከባድ የአካል ጉዳት አስከትሏል” ያሉት ሀይሉ “የአላማጣ የሰላም ጥሪ ችላ ሊባል አይችልም” ብለዋል። 

የአማራ ክልል መንግስት በሚያዝያ ወር በሰጠው መግለጫ ህወሓት የፕሪቶሪያን ስምምነት “ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር እና የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ” ጠይቋል።

በአንድ ወር በፊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ በደቡባ ትግራይ ራያ መፍፍረስ ያለበት አስተዳደር መፍረሱን እና በስፍራው የነበሩ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን  አስታውቀዋል

“አሁን ትኩረታችን ቀሪዎቹ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ እንዲያልቁ ማድረግ ነው” ብለዋል።

ይሁን እንጂ  ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ “በምዕራብ ትግራይ ፌዴራል መንግስት በኩል ምንም አይነት የሚታይ እንቅስቃሴ” አለመኖሩን በመተቸት፤ “ምንም እንቅስቃሴ አልተደረገም በሚል ቀጣዩ ክረምት እንዲያልፍ አንፈቅድም፣ የዚህም ተባባሪያቸው አንሆንም” ሲሉ ገልጸዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ኃይሎች በአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ “ገርጃሌ” እና “በቅሎ ማነቂያ” ከተባሉ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል

አቶ ጌታቸው የትግራይ ሀይሎች ከመንደሮቹ ለቀው እንዲወጡ ከአከባቢው ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል እንዲሁም ከፌደራል መንግስቱ እና ከአማራ ክልል መንግስት ጋር የተደረሰውን መግባባት በማክበር መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ ስታንዳርድ በትግራይ ክልል በኩል ያለውን አስታየት ለማካተት የደቡብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስን ለመግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካለትም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button