ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ ሳምንት ሁለት አመራሮች 'በታጠቁ አካላት' ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ ሳምንት ሁለት አመራሮች ‘በታጠቁ አካላት’ ተገደሉ።

በክልሉ የሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ትላንት ግንቦት 29፣ 2016 በታጠቁ ሰዎች መገደላቻቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል። 

ነፍሰጡር የነበሩት የወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊዋ፤ ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ “በፅንፈኛ አካላት” በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

“ቡድኑ በፅንፈኛነት በመቆም እናትነትን ከነፍሰ ጡርነት ጋር የተሸከመችን እንስት በጥይት ደብድቦ በመግደል የአሸባሪነቱን ዳርቻ ገልጿል” ሲል ከሷል። 

በተመሳሳይ መልኩ በያዝነው ሳምንት ነበር በዞኑ የሚገኘው ኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የተገደሉት። 

የኤፍራታ ግድም ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ “ፅንፈኛ” ሲል የጠራቸው አካላት፤ “በምሽት ተሹለክልከው በመግባት አስተዳዳሪውን ህይወት ቀጥፈውታል” ሲል ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።

የተገደሉት አስተዳዳሪው አቶ አልብስ በአከባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ የወደሙ የጤናና ሌሎች ተቋማትንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመስራት መልሶ ለማቋቋም ጥረት እያደረዱ የነበረ መሪ ነው ሲል ወረዳው ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአማራ ክልል በመንግስት ኃይሎች እና በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በረካታ ጥቃቶች እና የአመራሮች ግድያ ተፈጽመዋል። 

በተያዘው ሳምንት በክልሉ ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል

በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዲሁም የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ በሚኖርበት ቤት ላይበመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ በተነገረው ጥቃቶች የሰዎች ሕይወት እንዳላለፈ ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሰኔ ወር በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ ሁለት የተለያዩ የመንግስት የፀጥታ ዘርፍ የስራ ሃላፊዎች መገደላቸው አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ሰኔ 29 ቀን በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተደግለዋል፡፡ 

በተጨማሪም የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው በተለያያ ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ይታወሳል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ግርማ የሺጥላ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button