ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እንዲቋጭ የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 21/ 2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ሰላም እንዲሰፍን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ነሐሴ 19 ቀን 2016 በሰሜን ሻዋ ዞን በሱሉልታ እና ጭንጮ ከተሞች ባካሄዱት ሰልፎች ጠየቁ።

ሰሞኑን በሰሜን ሻዋ ዞን የሚገኙ በርካታ ወረዳዎች በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት ተቋጭቶ ሰላም እንዲሰፍን የሚጠይቁ ህዝባዊ ሰልፎች ተካሄደዋል።

ሰልፎቹ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ልጆች እና ሴቶች ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አንድ ላይ በመሰባሰብ ተካሄደዋል።

ትላንት በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተሳተፈው የጫንጮ ከተማ ነዋሪ የሆነው ተስፋዬ ገቢሳ፤ በእነዚህ ሰልፎች ባህላዊ  ስርዓቶች ያላቸውን ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

በሰልፎቹ ቀንበር የተሸከሙ ታዳጊዎችን፣ የቆሙ ፈረሶች እና ቀንበር የተሸከሙ ላሞች እና የመሳሰሉ ለየት ያሉ ትዕይንቶች ተካተዋል ሲል ነዋሪው ገልጿል። 

“በሰልፎቹ  ላይ ለስድስት ዓመታት የደረሱብን ስቃይና ጥቃቶች  እንዲያበቃ ጸልየናል” ብሏል።

አክሎም ሰሜን ሸዋ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የፌዴራል መንግስት እና የፋኖ ታጣቂዎችን መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት ጉዳት እየተደረሰበት መሆኑን ተናግሯል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“በተለይም የሱሉልታ ነዋሪዎች በእነዚህ ሶስት ተዋጊ አካላት መካከል ባለው ግጭት ተክጀበዋል። በምላሹም ነዋሪዎች ወደ ጎዳናዎች በመውጣት የግጭት ተሳታፊ ወገኖች ትጥቃቸውን ፈተው እርቅ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል” ብለዋል።

ሌላኛው በሰልፉ የተሳተፉት የጫንጮ ከተማ ነዋሪና የሃይማኖት መሪ ጃለታ አስፋው፤ በሰሜን ሸዋ ያለው ግጭት የዕለት ተዕለት ህይወትን ማስተጓጎሉን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

“እንቅስቃሴ፣ ንግድ፣ ትምህርት፣ ግብርና፣ ጤና አጠባበቅ እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በወታደራዊ እገዳዎች ተስተጓጉለዋል” ሲል አብራርቷል። የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች ተፋላሚ ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል ብለዋል። 

ባለፈው ሳምንት ወረ ጃርሶ፣ ደጋም፣ ደብረ ሊባኖስ፣ ኩዩ፣ ያያ ጉላሌ እና የተለያዩ ቀበሌዎችን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ሰላም ጥሪ መደረጉን  አክለው ጠቁመዋል።

“በሱሉልታ እና በጫንጮ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፤ ፈረሶች እና የተጠመዱ ላሞችን እንዲሁም እንደ ከለቻ፣ ጫቹ እና ሳር የመሳሰሉ ባህላዊ ቁሶችን በመያዝ በትናትናው ዕለት በሱሉልታ እና በጫንጮ ከተማ ግጭት እንዲቆም በህዝባዊ ሰልፍ ጥይቀዋል” ሲሉ ነዋሪው ተግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በኦሮሚያ ክልል የተካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ “ገዢው ፓርቲ የተወሰኑ ሰዎችን በማነሳሳት የሰሜን ሸዋ ህዝብ የሰላም ጥሪ እያቀረበ በማለት ላይ ነው” ብሏል። 

ብድኑ በመግለጫው የኦርሞ ነጻነት ሠራዊትም ሆነ የኦሮሞ ህዝብ ሰላም እንደሚሻ በመግለጽ፤” ከሁለት አመት በፊት ገዢው ፓርቲ ከሽብርተኞች ጋር የሰላም ድርድር አናደርግም ቢልም ኦነስ ለሰላም ቁርጠኛ ነው” ሲል ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button