ዜናፖለቲካ

ዜና: “በክልሉ የተፈጠረው የፖለቲካዊ ልዩነት ወደ ጸጥታ ስጋት እንዳይቀየር በትኩረት እየሰራን ነው” ሲሉ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/2016 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንትና የሰላምና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ “በክልሉ የተፈጠረው የፖለቲካዊ ልዩነት ወደ ጸጥታ ስጋት እንዳይቀየር በትኩረት እየሰራን ነው” ሲሉ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ነሃሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

“በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ፖለቲካዊ የሆኑትን ጨምሮ ሌሎች አበይት መድረኮች ያለምንም የጸጥታ ችግር ተካሂደው መጠናቀቃቸውን” ገልጸው ቀጣይ በአላትም “በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች በሰላም እንዲካሄዱ እና እንዲጠናቀቁ ዝግጅት አድርገናል” ብለዋል።

“የክልሉን ጸጥታ የሚያደፈርስ ችግር ሊያጋጥም አይችልም” ሲሉ ገልጸዋል።

የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት “እንዴት ሊፈታ እንደሚችል፣ ወደ መልካም አጋጣሚ እንዴት መቀየር ይቻላል በሚል ትኩረት አድርገን ነው እየሰራን ያለነው” ብለዋል።

ልዩነት የፈጠሩ አመራሮች “ልባቸውን አሳድገው ልዩነታቸውን በፖለቲካዊ አግባብ እንዲፈቱ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የጸጥታ ሀይሉ “ገለልተኛ ሁኖ የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚቆም” አስታውቀው “የጸጥታ ሀይሉ ለፖለቲካ ስራዎች፣ ፖለቲካው ደግሞ ለጸጥታ ስራዎች ምቹ ሁኔታዎችን ሊፈጥሩ ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል።

በትግራይ ፖለቲካ “የትግራይ ተወላጆች ብቻ የሚሳተፉበት እንጂ ከውጭ ጣልቃ የሚገባ እጅ እንዳይኖር” እየሰራን ነው ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የትግራይ ህዝብ ከልክ በላይ የሆነ ችግር ተሸክሞ ነው ያለው ያሉት ሌተናል ጀነራሉ ለተጨማሪ ችግሮች እንዳይዳረግ የሚቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

“ቀይ መስመር ናቸው ያልናቸው ሁኔታዎችን አሉ” “በሀይል በተሸጋገረ መልኩ ነገሮች ለመፍታት መሞከር” ሲሉ የጠቆሙት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ይህ አይነቱ ሁኔታ “አሁንም ዝግ” ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

“እነዚህ እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሁሉም የትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ትብብር አለ፣ ሊቀጥልም ይገባዋል” ብለዋል።

ሌላኛው ሌተናል ጀነራል ታደሰ በመግለጫቸው ያነሱት ጉዳይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱን ሂደት ሲሆን በመግለጫቸው ተፈናቃዮች በተመለሱት አካባቢዎች ተገቢውን የጸጥታ ስራዎችን በመስራት ዙሪያ ክፍተት እንዳለ ጠቁመዋል።

ይህ የሆነበት ምክንያትም “በአከባቢው የነበሩ የጸጥታ ሃይሎች ተቀናጅተው እየሰሩ ስላልነበረ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ይህንን በመከታተል ረገድ ተዘናግቶ ስለነበረ ነው” ብለዋል።

ወደ ቀያቸው የተመለሱ ነዋሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ እና የሚያስተዳድሩትን እንዲመርጥ ለማስቻል መከላከያ ሀይሉ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ተፈናቃዮች በተመለሱባቸው አከባቢዎች በተለይም በጸለምት አከባቢ የተመቻቹ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ፣ አስተማማኝ ሰላም እስኪሰፍን፣ በአከባቢዎች በሚካሄደው የጊዜያዊ አስተዳደር ምርጫ እንደማንሳተፍ በግልጽ አቅጣጫ አስቀምጠናል ማለታቸውን ከድምጽ ወያነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button