ማህበራዊ ጉዳይቢዝነስዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በ2016 በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያት ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል - ኢሰመኮ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም፡- በ2016 ዓ.ም በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው 3ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዳሷል። በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች የትጥቅ ግጭቶች፣ ጥቃቶች ወይም የጸጥታ መደፍረሶች ሁነቶች መከሰቱን የጠቆመው ኮሚሽኑ በታጣቂ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል ካለው የጸጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ፣ ‘ወቅታዊ ጉዳይ’ በሚል ምክንያት ሰዎችን በተለይ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እስር፤ በክልሉ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ቡድን ትረዳላችሁ በሚል ሰዎችን በጅምላ ማስር፤ እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብታችውን ማገድ ታይቷል ብሏል።

በተለይም በክልሎች ውስጥ በማኅበራዊ ሚድያ በሚያጋሩት መልዕክት “የመንግሥት ኃላፊዎችን ስም አጥፍተዋል፣ ግጭት ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል በሚል የሚታሰሩ ሰዎች” መኖራቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስታውቋል።

በአብነትም በአፋር ክልል በ2016 ዓ.ም. ለ6 ወራት ያክል በእስር ላይ የቆዩ እና በማኅበራዊ ሚድያ ላይ መንግሥትን የሚቃወም ሐሳብ አስተላልፋችኋል በሚል ምክንያት የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን አካቷል።

የመንቀሳቀስ መብትን በተመለከተ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ሁኔታ ወይም በሌላ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች ምክንያት በተለይም በመንገድ የሚደረግን እንቅስቃሴ አዳጋች እንደነበር አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአማራ ክልል በየኬላው በመንግሥት የጸጥታ አካላት፣ እንዲሁም በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች አስገዳጅ ፍተሻ ይደረግ እንደነበር የጠቆመው ኢሰመኮ በሌላ በኩል በመንገድ ላይ ድንገት የተኩስ ልውውጥ ያጋጥም እንደነበር አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት “አብዛኛው ማኅበረሰብ እጅግ አስገዳጅ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር በመንገድ የሚጓዙ የትራንስፖርት አማራጮችን አይመርጥም ብሏል።

በትጥቅ ግጭቱ ሳቢያ በክልሉ የነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረው እጥረት ተከትሎ፣ ነዳጅ በጥቁር ገበያ የሚሸጥ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ክፍያን እጅግ እንዲንርና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዲፈጠር አድርጓል።

በ2016 ዓ.ም በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወይም በታጣቂ ቡድኖች ለተከታታይ ቀናት ወይም ለአጭር ጊዜ የሚዘጉ መንገዶች ምክንያት በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች መከሰታቸውን፣ በሸቀጦች ዋጋ እና በገቢ ላይ እንዲሁም በጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ተደራሽነት ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መበራከታቸውን አመላክቷል።

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በግጭት ያሉ እና በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የጸጥታ እና የኢኮኖሚያ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ ወይም መቆም በአዋሳኝ ክልሎች ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል ሲል ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስታውቋል። ለአብነትም በአፋር እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጤና እና የምግብ ሸቀጦች እጥረት እንዲሁም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን አስቀምጧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button