Uncategorized
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: “ቢሮ ስንገባ የኢትዮጵያ ጂዲፒ 86 ቢሊየን ዶላር ነበር፣ ዛሬ ግን 205 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፤ 6ቱ ጎረቤት ሀገራት ተደምረው የእኛን ጂዲፒ አያክሉም - ጠ/ሚኒስትር አብይ

ዜና: “ቢሮ ስንገባ የኢትዮጵያ ጂዲፒ 86 ቢሊየን ዶላር ነበር፣ ዛሬ ግን 205 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፤ 6ቱ ጎረቤት ሀገራት ተደምረው የእኛን ጂዲፒ አያክሉም – ጠ/ሚኒስትር አቢይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እያካሄደው በሚገኘው መደበኛ ስብሰባው ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፤ አያይዘውም የመንግስታቸውን የበጀት አመቱን አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

ለሰዓታት በዘለቀው የመጀመሪያው ክፍል ምላሽ እና ማብራሪያቸው በአጠቃላይ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ዳሰዋል።

በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) በእጥፍ አድጓል ሲሉ ገልጸዋል።

እኛ ወደ ቢሮ ስንገባ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) 86 ቢሊየን ዶላር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ግን 205 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

ከለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ትልቁ ኢኮኖሚ እንደነበራት አስታውሰው ዛሬ ግን 6ቱ ጎረቤት ሀገራት ተደምረው የእኛን ጂዲፒ አያክሉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት የወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ በአጠቃላይ ከለውጡ በኋላ 23 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከሁሉም ዘርፎች ማመንጨት ተችሏል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከገቢ ምርቶች በነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ዕዳ ክፍያ አንጻር በዓመት 7 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዓመት መንግስት 529 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት 11 ወራት 466 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል ሲሉም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የነበረባት እዳ ወደ ልጆቻችን መሸጋገር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት ዛሬ ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ከጂዲፒ ዝቅ ብሏል፤ ይሄም ትልቅ ድልና ትልቅ ዜና ነው ሲሉ ተደምጠዋል፤ ባለፉት አመታት ሳንበደር ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ከዚህ ቀደም ተበድራችሁታል የተባለ ሀብት ስንከፍል ቆይተናል ሲሉም ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ12 ሺህ 800 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር አብይ ባንኮች ከሚያቀርቡት ብድር ከ80 በመቶ በላይ የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ነው ሲሉ ገልጸው ይህም የፋይናንስ ዘርፉ በጤናማ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ቢሆንም ነገር ግን ባንኮች ከሀገር ውስጥ ባለፈ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን ከወዲሁ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ
Back to top button